​የአሰልጣኞች አስተያየት | ኢትዮጵያ ቡና 0-2 ሀዋሳ ከተማ

ከአስረኛው ሳምንት የአስር ሰአት ጨዋታ በኋላ ተጋጣሚ አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡

አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ – ኢትዮጵያ ቡና 

ስለ ጨዋታው

“በውጤቱ ተሸንፈናል ከእኛ ኃላ ያሉ ኳሶች ሲበላሹ ያንን ቦታ እንዳይጠቀሙ ምን ማድረግ አለብን በሚለው ተነጋግረናል የመጀመሪያው ኳሶች እንዳይበላሹ ያን ቦታ ሊጠቀሙ ስለሚችሉ ያን ቦታ እንይጠቀሙ በተገቢው ሁኔታ አልሰራንም በዚህም ምክንያት ጎሎችን ሊያገኙ ችለዋል፡፡

አንድ ተጫዋች ብቻ ስለመቀየራቸው

“ተቀያሪ ተጫዋች እንግዲህ ለአሰልጣኝ አማራጭ ነው፡፡አጠቃላይ የነበረው ነገር በተለይ ኳስ ስነናገኝ ከፊት ያሉት የነሱ ተመልሰው ከኋላ ያግዛሉ እነዚህ ተጫዋች አሉ ቦታውን ይዘጋሉ፡፡ያንን ቦታ እንደቡድን እንዴት ማረም አለብን የሚለው ነው ያንን ደግሞ ማረም አልቻልንም ይህንንም ማድረግ ባለመቻላችን ተሸናፊ ሆነናል፡፡

ከፊት መስመር ስለነበረው ድክመት

“ከማንኛውም ቡድን ጋር ስንጫወት ከተጋጣሚ ቡድን ጎል ማግኘት ለእኛ ከባድ ነው፡፡ይሄም ሊቀጥል ይችላል መስረት ማሻሻል ያለብን ነገር ነው፡፡በቀላሉ አሁንም አሁንም ክፍት ቦታዎችን ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ያንን ነገር ማስተካከል እንዳለብንም ይሰማኛል።”

አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ – ሀዋሳ ከተማ

ዕቅዳቸውን ስለመተግበራቸው

“መጀመሪያም ያሰብነው በሁለት አይነት መንገድ ለመጫወት ነው፡፡አንደኛ ከአስራ ስድስት ከሀምሳ ፕረስ ለማድረግ ነው፡፡እሱን ትተን እንደገና ከተከላካይ አማካይ ፕረስ ለማድረግ ሞከርን ከሱም በዛው ለማስቀጠል ነው ያሰብነው በዚህም መንገድ በተለይ ከእረፍት በፊት ጥሩ ኳሶችን አግኝተናል መጠቀም አልቻልንም ዞሮ ዞሮ ያንን አስጠብቀን ከእረፍት መልስ ከእረፍት በኋላ ጎሎችን እንደምናገኝ ስለተረዳን በዛው መንገድ ነው ዘጠናውን ደቂቃ ለመጠቀም ያሰብነው እንዳሰብነውም ተሳክቶልናል፡፡

ቡድኑ በቀጣይ ይህን ውጤት ስለማስቀጠሉ
አዎ እቅዳችን እንደዛ ነው፡፡በየቲሙ መዘጋጀት አለብህ እያንያንዱ ቡድን ይዞ የሚመጣው አጨዋወት አለ በዛ መንገድ እየተዘጋጀን እንመጣለን እንደዛሬ ሸሽተን ሳይሆን በጣም ፕረስ አድርገን ውጤታማ ለመሆን ነው ሀሳባችን፡፡