
ሲዳማ ቡና ከአንድ ተጫዋች ጋር ተለያይቷል
ኬኒያዊው የመስመር አጥቂ ከሲዳማ ቡና ጋር በመለያየት በይፋ ለሀገሩ ክለብ ፈረመ፡፡
ሲዳማ ቡናን በያዝነው የውድድር ዓመት መጀመሪያ ከተቀላቀሉ የውጪ ዜግነት ካላቸው ተጫዋቾች መካከል ኬኒያዊው የመስመር አጥቂ ፍራንሲስ ካሀታ አንዱ ነው፡፡
ተጫዋቹ በአንድ ዓመት ውል የታንዛኒያውን ሲምባ ክለብ በመልቀቅ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ ለሲዳማ ቡና ፊርማውን በማኖር የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በሀዋሳ ሲደረግ አብዛኛዎቹን ጨዋታዎች በተጠባባቂ ወንበር ላይ አሳልፏል።
ፍራንሲስ ካሀታ ከሲዳማ ቡና ጋር ቀሪ የስድስት ወራት ውል የነበረው ቢሆንም በግልፅ የተለያየበት ምክንያት ባይታወቅም ወደ ትውልድ ሀገሩ ኬኒያ ተመልሶ በዛሬው ዕለት ለኬኒያው ፖሊስ ክለብ የአንድ ዓመት ውል መፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
ተዛማጅ ፅሁፎች
የአሰልጣኞች አስተያየት | መከላከያ 0-0 አዳማ ከተማ
የሳምንቱ ማሳረጊያ ጨዋታ ያለ ጎል ከተጠናቀቀ በኋላ አሰልጣኞች ድህረ ጨዋታ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ - መከላከያ ስለ ጨዋታው...? "በመጀመሪያው...
ሪፖርት | መከላከያ እና አዳማ ያለግብ ተለያይተዋል
28ኛው ሳምንት ደካማ ፉክክር በታየበት እና 0-0 በተጠናቀቀው የመከላከያ እና አዳማ ከተማ ጨዋታ ተቃጭቷል። መከላከያ ከወላይታ ድቻ ያለግብ ከጨረሰበት ጨዋታ...
የአሰልጣኞች አስተያየት | ፋሲል ከነማ 1-0 ሀዋሳ ከተማ
ፋሲል ከነማዎች ወሳኝ ድል ካስመዘገቡበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል። አሰልጣኝ ኃይሉ ነጋሽ - ፋሲል ከነማ...
ሪፖርት | ዐፄዎቹ ከመሪው ያላቸው የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ ቀንሰዋል
እጅግ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን የፋሲል ከነማ እና የሀዋሳ ከተማ ጨዋታ ፋሲሎች በመጂብ ቃሲም ብቸኛ ግብ በድል መወጣታቸውን ተከትሎ ከቅዱስ ጊዮርጊስ...
የአሠልጣኞች አስተያየት | አርባምንጭ ከተማ 1-0 ኢትዮጵያ ቡና
በአህመድ ሁሴን ብቸኛ ግብ አርባምንጭ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን ከረታበት ጨዋታ በኋላ አሠልጣኞች አስተያየት ሰጥተዋል። መሳይ ተፈሪ - አርባምንጭ ከተማ ስለተከታታይ...
ሪፖርት | በአቡበከር የመጨረሻ ጨዋታ አዞዎቹ ቡናማዎቹን ረተዋል
አርባምንጭ ከተማዎች በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት ተከታታይ ጨዋታዎችን ያሸነፉበትን ውጤት ኢትዮጵያ ቡና ላይ አስመዝግበዋል። ባሳለፍነው ሳምንት ከድሬዳዋ ከተማ ሦስት...