​የወልቂጤ ከተማ ክስ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል

ወልቂጤ ከተማ በፍቀረየሱስ ተወልደብርሀን ላይ ያነሳው ጥያቄ ላይ ምላሽ አግኝቷል።

በአስረኛው ሳምንት የሊጉ መርሐ-ግብር ሀድያ ሆሳዕና እና ወልቂጤ ከተማን  ያገናኘው ጨዋታ 2-2 በሆነ አቻ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል። በዚሁ  የ2014 የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር 10ኛ ሳምንት ጨዋታ የሀድያ ሆሳዕናው  ፍቅረየሱስ ተወልድብርሃን በዘጠኝ ሳምንት ውስጥ በአጠቃላይ ያተመለከተው ቢጫ ካርድ አምስት ደርሷል በማለት ወልቂጤ ከተማ ጥያቄ አንስቶ ነበር። ሆኖም ክለቡ ለሊግ ካምፖኒው የላከውን ኩሚኒኪ መሰረት ያደረገው ይህ ክስ ዳር ሳይደርስ ቀርቷል።

ለዚህም ምክንያት የሆነው ፍቅርየሱስ ተወልደብርሃን ከአርባምንጭ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ በሁለት ቢጫ ከሜዳ በመወገዱ እና በዚህም የአንድ ጨዋታ ቅጣት ተጥሎበት ከአዳማ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ ከሀድያ ሆሳዕና ከስብስብ ውጭ በመሆኑ ነው።

የሊግ ካምፓኒው የውድድር እና ሥነስርዓት ኮሚቴ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ወገኔ ዋልተንጉስ ለሶከር ኢትዮጽያ እንደገለፁት ተጨዋቹ  በሦስተኛው ሳምንት ያየው በአንድ ጨዋታ ሁለት ቢጫ በመሆኑ እና ቅጣቱን በማጠናቀቁ አሁን ያለበት ሦስት ቢጫ ብቻ ሆኗል። ኃላፊው ችግሩ የተፈጠረው ኮሚኒኪ የሚዘጋጀው ሶፍርትዌር ሁሉንም ቢጫ ካርድ በነጠላ ስለሚቆጥር በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት እንዴለለው ከወልቂጤ አመራሮች መግባባታቸውን ነግረውናል። በወቅቱ ተጫዋቹ የተላለፈበትን ቅጣትም በሦስተኛው ሳምንት ኮሚኒኬ ማሳወቃቸውን ጨምረው አስታውሰዋል። 

ያጋሩ