ድሬዳዋ ከተማ ወደ ዝውውሩ ገብቷል

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፉት ድሬዳዋ ከተማዎች ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ የሁለት ነባሮችን ውልም አድሷል።

በአሰልጣኝ እዮብ ተዋበ መሪነት ያለፉትን ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የተሳተፉት ድሬዳዋ ከተማዎች ለቀጣዩ ዓመት የሊግ ተሳትፎው ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት ክፍተት አለብኝ ባላቸው ቦታዎች ላይ ወደ ዝውውሩ በመግባት ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ የሁለት ነባሮችን ውል አራዝመዋል።

ክለቡን ከተቀላቀሉ ተጫዋቾች መካከል የቀድሞዋ የመቻል ፣ ዳሽን ፣ ጌዲኦ ዲላ እና የተጠናቀቀውን ዓመት በአዲስ አበባ ቆይታ የነበራት ተከላካዩዋ ፋሲካ በቀለ ፣ በደደቢት ፣ ዳሽን እና አዳማ የተጫወተችው አጥቂዋ ሰርካዲስ ጉታ ፣ በሀዋሳ እና መቻል ተጫውታ ወደ ቀድሞው ክለቧ የተመለሰችው ተከላካዩዋ አይናለም አደራን ጨምሮ ሰላማዊት ለገሠ አማካይ ከአቃቂ ፣ ሜሮን አለማየሁ አማካይ ከአቃቂ ፣ መታሰቢያ ታመነ ተከላካይ ከአቃቂ ፣ ዘይነባ ሰይድ አማካይ ከአዲስ አበባ እና ትዕግሥት ዘውዴ የመስመር አጥቂ ከአዳማ የክለቡ አዳዲሶቹ ፈራሚዎች ናቸው።

ክለቡ ከስምንቱ ፈራሚዎች በተጨማሪ የተከላካዮቹን መስከረም ኢሳያስ እና ፀሀይ ኢፋሞን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል።