የአሰልጣኞች አስተያየት | ጅማ አባ ጅፋር 1-0 አዲስ አበባ ከተማ

ጅማ አባ ጅፋር አዲስ አበባ ከተማን 1-0 ከረታበት ጨዋታ በኋላ አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል፡፡

አሰልጣኝ ደምሰው በፍቃዱ – አዲስ አበባ ከተማ

ስለ ሽንፈቱ

“ጨዋታው በእርግጥ እኔ እንደጠበኩት አይደለም ምክንያቱም የተሻለ ነገር እንጫወታለን ብልጫ እናገኛለን ብለን  ነበር ፤ ግን እንደጠበኩት አልሆነም። በእርግጥ የጎል ዕድልን በደንብ ፈጥረናል። በተደጋጋሚ ብዙ ቀርበናል ወደ ጎል መቀየር  ነው ያልተቻለው። ይሄ ደግሞ በኳስ አጋጣሚዎች ሁሉ የሚኖር ነው፡፡አስተካክለን ለመቅረብ ነው የምንሞክረው፡፡

ነጥቡን ያጣችሁን በተጋጣሚው ወይንስ በእናንተ ድክመት

“በእኛ ድክመት ነው፡፡ በተቃራኒ አይደለም ያን ያህል ተጭነውን ተከላካዮችን ፈትነው የተገኘ ነገር አይደለም። እንደምታየው ደግሞ አንዳንድ ጊዜ እዛ አካባቢ ቅጣት ምት ያሰጣል አያሰጥም ሌላ ጥያቄ የሚያስነሳ ሆኖ ሆኖም ግን በእኛ ድክመት ሦስት ነጥብ አግኝተዋል፡፡

ጅማ የመጀመሪያ ድሉን በእናተ ላይ ስለማሳካቱ 

“በእግርኳስ ጨዋታ እኮ ይሄ መጀመሪያ ሊከሰት እንደሚችል እናምናለን። ጅማ መጨረሻ ስለሆነ አያሸንፍም ማለትም አይደለም። ኳስ እንግዲህ ከእንቅስቃሴ ባሻገር ሁኔታዎች የሚፈጥሩት ነገር ይኖራል፡፡ ያንን ተጠቅመው ሦስት ነጥብ አግኝተዋል፡፡ለእነርሱ ይሄ ይጠቅማል አይጠቅምም የሚለው ወደፊት የሚታይ ነው፡፡”

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ – ጅማ አባጅፋር

ስለጨዋታው

“ጨወታው ጥሩ ነው፡፡ ይህች የጓጓንላት ሦስት ነጥብ አግኝተናል፡፡ እንሞክራለን፡፡

ከአስር ሳምንት በኋላ የመጀመሪያ ድል ስለማሳካት

“በእንቅስቃሴ እስከ አሁን ያነስንባቸው ጨዋታዎች የሉም። ምናልባት ከባህር ዳር ጀምሮ ሰበታ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድኑ ያሳየው ውጤቱ እንደዚህ የዘቀጠ ነው ብሎ ማሰብ ከባድ ነው፡፡ ግን ተጋጣሚያችንም እንደወትሮ አይደለም። ቀዝቀዝ ያለ ነገር አለው። ግን ቡድኑ ከነበረበት ውጥረት አኳያ ስታየው ለእኛ መልካም ነው፡፡

የዛሬው ውጤት መነሻው ምን ነበር

“ኳሶችን ሳይጨናነቁ ተረጋግተው እንዲጫወቱ ነው፡፡ ምክንያቱም ውጤት ስታጣ ከአሰልጣኙ የበለጠ ተጫዋቾቹ ይጨነቃሉ። ስለዚህ በኳሱ እንዲደሰቱበት ነበር ፍላጎቴ። ልጆቹ እንደወትሮውርሱም አይተህ ከሆነ ፈጣሪ ረድቶን የልጆቼን ድካምም አይቶ ነጥብ አግኝተናል፡፡