አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል የነገውን ጨዋታ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

👉 “ተቀያሪ ተጫዋቾቼ ለኔ አማራጮቼ እንጂ ግዴታዎቼ አይደሉም”

👉 “እንደ ባለሙያ የምሰራውን አውቃለው”

👉 “እነዚህ ልጆች ሀገር ናቸው ሊደገፉ ይገባል”

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለኮስታሪካ የዓለም ዋንጫ ማጣርያ የአራተኛ ዙር የመልስ ጨዋታውን ነገ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከታንዛንያ አቻው ጋር ነገ ከሚያደርገው የመልስ ጨዋታ አስቀድሞ አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ወሎ ሠፈር በሚገኘው የፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በርከት ያሉ የሚዲያ አካላት በታደሙበት በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ብሔራዊ ቡድኑ ከታዛንያው ጨዋታ በኋላ በአዲስ አበባ የነበረውን የዝግጅት ሁኔታ ውጤቱን መቀልበስ በሚቻልበት መንገድ ዙርያ ጠንከር ያለ ስራ ይሰሩ እንደነበረ መጠነኛ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማስከተል ከጋዜጠኞች በርከት ያሉ ጥያቄዎች የቀረበላቸው ሲሆን በዋናነት የተነሱ ጥያቄዎች እና ምላሾቻቸውን እንዲህ አቅርበነዋል።

በታዛንያው ጨዋታ ተቀይረው በመግባት ጥሩ እንቅስቃሴ ያደረጉ ተጫዋቾች አስቀድመው ያልገቡበት ምክንያት ?

” ይህ የሙያ ጥያቄ ነው። እኔ ደግሞ እንደ ባለሙያ የምሰራውን አውቃለው። አረጋሽ የሴካፋ ዋንጫን ስናነሳ አልነበረችም። ይህ ማለት ቡድኑ በታክቲክ ብቻ ሳይሆን በስትራቴጂ ነው። የተጫዋች አቅም የምናቀው በቅርብ ያለን ባለሙያዎች ነን አንድ ተጫዋች ተቀይሮ ገብቶ ጥሩ ሊሆን ይችላል። ተቀያሪ ተጫዋቾቼ ለኔ አማራጮቼ እንጂ ግዴታዎቼ አይደሉም። በወቅታዊ አቋም የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረገ ተጫዋች እናስቀድማለን። በዘመናዊ እግርኳስ ተጠባባቂ ቋሚ ተሰላፊ የሚባል ተጫዋች የለም። ሜዳ ገብቶ ጥሩ መስራት እና ሀገርን ማገልገል የተሻለ ነገር ነው።”

አጋጣሚዎችን ያለመጠቀም ክፍተት በታንዛንያው ጨዋታ መኖሩ በቀጣይ ይህን ለማስተካከል ምን ታስቧል ለተባለው ?

” ምንም ጥርጥር የሌለው ትክክለኛ ጥያቄ ነው። እኛም እንደ ባለሙያ ያየነው ነው። ያም ቢሆን እነዚህ ልጆች የመጡበትን መንገድ ማሰብ ተገቢ ነው። ብዙ ጨዋታ አድርገው የመጡ በመሆናቸው ጉልበት የመጨረስ ነገር ይታያል። ይህ ቡድን አስራ ሁለት ሲዳርግ ጎል ያላስቆጠረው ታንዛንያ ላይ ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ላይ ከአንድ ጎል በላይ እያስቆጠረ የመጣ ስለሆነ በአጨራረስ ልንሳሳት እንችላለን ወጣቶች እንደመሆናቸው መጠን ስህተት ይፈጠራል። እንኳን እነርሱ ትልልቅ ተጫዋቾች ጎል ሊስቱ ይችላሉ። እነርሱም እያስተካከልን የሙያ እገዛ እያደረግን እንሄዳለን።

ቡድኑ እያስመዘገበ ካለው ስኬት አንፃር ከመንግስት ምንም አይነት ድጋፍ ለተጫዋቾች አለመደረጉ በልጆቹ ላይ የፈጠረው ተፅእኖ አለ ?

” ይህን ጥያቄ እኔ ከመምመልሰው ይልቅ እናተ ብትመልሱት ይሻላል ብዬ አምናለው። ከዚህ ቀደም በወንዶቹ የሴካፋ ዋንጫ አምጥተው በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻውም አስራት ኃይሌ ጊዜ ምን አይነት ሽልማት እንደተሸለሙ ይታወቃል። ይሄን የምናገረው ከጥቅም አንፃር አይደለም። ልጆቹ በምስጋና ቢደገፉ የተሻለ ነው። ከስጦታ ይልቅ ትልልቅ የመንግስት ከፍተኛ የሴት አመራሮች ከስራ ድርሻቸው አንፃር መጥተው ማነቃቃት አለባቸው ብዬ አምናለው። ይህን ነገር ግን በሴቶች አላየሁም። የወጣቶች ስፖርት ሚኒስቴር መጥቶ ልጆቹን ደግፏል ይህ ይበል የሚያሰኝ ነው። ይህ ቡድን የፌዴሬሽኑ ብቻ አይደለም። እነዚህ ልጆች ሀገር ናቸው። ፌዴሬሽኑ ብቻ ነው የሸለመው አይዟቹሁ ብሎ የደገፈው ሌሎች ተቋማት ሲያበረታቱ ሸልሙ አላየንም። በቀጣይ እነዚህ ልጆች መጥተው ቢያበረታቱ ጥሩ ነው።

ከተከታታይ ድል የመጣ ቡድን ነው ባለፈው ሽንፈት አስተናግዷል በዚህ በኩል የልጆቹ አምሮ ላይ ምን ተሰርቷል ?

“ይህ ቡድን በአስራ አንድ ጨዋታ ሽንፈት አያቅም። ሽንፈት ሲመጣ ልጆቹ መቀበል አቅቷቸው ሲያለቅሱ ሳፅናና ነበር። ምክንያቱም ልጆቹ በሀገር ጉዳይ አይደራደሩም ሲያለቅሱ ነበር። ከዛ በኃላ በስነልቦናው በክፈል ትምህርት ስሰጥ ነበር።ከሽንፈቱ እራሳቸውን አስተካክላቹ ሜዳችን ላይ ውጤት መቀልበስ ትችላላቹሁ በማለት ብዙ ስራ ሰርተናል። ነገም የተሻለ ውጤት ይዘው እንደሚወጡ አስባለው።

ከባለፈው ጨዋታ ለነገው ጨዋታ በጉዳት ምክንያት የማይጫት ተጫዋች ይኖራል ?

“አንድ ሁለት ሦስት የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋቾች ጉዳት ላይ ይገኛሉ ። ይህን ደግሞ የኔ ሳይሆን የህክምና ባለሙያዎች የሚወሰን ስለሆነ ነው። ነገ ነው እኔ የማረጋግጠው። ለምሳሌ ናርዶስ ጌትነት ህመም ላይ ነው ያለችው ትጫወታለች አትጫወትም የሚለውን ነገ የሚታወቅ ይሆናል።”