የአሰልጣኞች አስተያየት | ባህር ዳር ከተማ 0-2 ቅዱስ ጊዮርጊስ

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

በምሽቱ ተጠባቂ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ባህር ዳር ከተማን ከረታ በኋላ አሰልጣኞቹ ለሱፐር ስፖርት ተከታዩን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ አብርሀም መላኩ – ባህር ዳር ከተማ

ስለ ጨዋታው መልክ

“ጨዋታው የሄደበት መልክ አንድ ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ የገባው ጎል ልጆቻችን ላይ ያልሆነ ስሜት እንዲመጣ አድርጓል። በተለይ በግብ ጠባቂያችን ላይ ጠንከር ያለ ነገር ወስዶበታል ማለት ይቻላል። ቀላል የሆነ ኳስ ሁለተኛ ጎል ተቆጥሯል። የመጀመርያው ጎል ተፅዕኖ ፈጥሯል ብዬ ነው የማስበው።

ስለ ተከታታይ ሽንፈታቸው

“ውድድሩ ጠንካራ እንደሆነ እየተመለከትነው ነው። እንግዲህ ሁለት ጨዋታ በተከታታይ ጥለናል በቀጣይ የነበሩትን ክፍተቶች አርመን በተሻለ መንገድ ለመቅረብ እንሞክራለን። ያው ጨዋታው እየሄደ የተወሰነ ማስተካከያ አድርገን ነበር። በተለይ ጎል ላይ ለመድረስ ከፍተኛ ስሜት ነበር። ግን የመጨረስ ሁኔታዎቹ በሚገባ ስላልነበሩ በመጀመርያው አጋማሽ መጨረሻ ላይ ያገኘናቸውን ወደ ጎልነት ብንቀይር ውጤቱ ይህ ባልነበር። ነገር ግን ተምረንበት ቀጣይ የተሻለ ነገር ለመስራት እንሞክራለን።

በዋንጫው ፉክክር አላቹሁ ማለት ይቻላል ?

ውድድሩ ገና ነው። ማስተባበያ ለማቅረብ ሳይሆን ገና አስራ ዘጠኝ ጨዋታ አለ በስንት ነጥብ ያልቃል ብለህ ብትጠይቀኝ እናቀዋለን። ስለዚህ እዛ አካባቢ ለመሆን ይከብዳል ብዬ አላስብም። አሁን እና ወደፊት የምንሰራቸው ስራዎች መጠንከር ካልቻሉ አደገኛ ሁኔታ ይፈጠራል ብዬ አስባለው። አሁንም ውድድሩ ላይ አለን።

ሊጉ በስንት ነጥብ ያልቃል

አስካሁን እንዳየነው ከስልሳ ነጥብ በላይ ሆኖ አላየነም። ቀሪዎቹን ጨዋታዎች አሁን ካለን ነጥብ ጋር ስትደምረው በዛ ማለቅ ከቻለ ፉክክር ውስጥ ነን ለማለት እንጂ እግርኳስ ነው የሚሆነው አይታወቅም። ከዛም በላይ ነጥብ ሊያልቅ ይችላል።

አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

የማሸነፋቹሁ ስኬት ምን ነበር

ህብረታችን ! ሜዳ ላይ አድርጉ የተባሉትን በማድረጋቸው ውጤቱን አግኝተነዋል።

ባለመሸንፍ ጉዞ ውስጥ ምን የሚቀራቹ ነገር አለ

አንዳንድ ስህተቶች አሉ። መረጋጋት እና የምናገኛቸውን የጎል ዕድሎች ያለመጠቀም ነገር አለ። እነዛን ነገሮች አስተካክለን የተሻለ ነገር ለመስራት ነው የምንሄደው

የቅዱስ ጊዮርጊስ ጥንካሬ ተመልሷል

ገና ነው። የቅዱስ ጊዮርጊስን ጥንካሬ ለማየት ቀን በቀን ነው የምንሰራው ፤ ገና ነው ውድድሩ አላለቀም። መጨረሻ ላይ ብንነጋገር ደስ ይለኛል።

የድሬደዋ ቆይታ

በፍቅር ተቀብለውናል ገና ውድድሩ አላለቀም። ሁለት ጨዋታ ተጫውተን ሁለቱን አሸንፈናል። ድሬ ፍቅር መሆኗን እያየን ነው። የተሻለ ነገር ለማድረግ ጠንክረን እንሰራለን።