[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ለደቡብ አፍሪካው ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ እንደፈረመ የተነገረለት አቡበከር ናስር ለነገው ጨዋታ ይደርስ ይሆን ?
አቡበከር ከቀናት በፊት የደቡብ አፍሪካው ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የሙከራ ጊዜ ሰጥቶት ወደ ስፍራው አምርቶ የተመለሰው አቡበከር ናስር የዝውውሩ ሂደት ምን መልክ አለው ስለሚለው ጉዳይ ግልፅ የሆነ መረጃ ባይኖርም ዝውውሩ እንደተጠናቀቀ የክለቡ የበላይ አመራሮች በተለያዩ መንገዶች መረጃዎችን እየሰጡ እንደሆነ ይታወቃል። ሶከር ኢትዮጵያ ከራሱ ከአቡበከር አንደበት የዝውውሩን አጠቃላይ ሁኔታ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት ብታደርግም ተጫዋቹ ቃለመጠይቅ ለመስጠት ፍቃደኛ ባለመሆኑ ምክንያት ጥረቷ ሳይሳካ ቀርቷል።
ያም ቢሆን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት እንዳገኘነው መረጃ ከሆነ ኢትዮጵያ ቡና እና ማሜሎዲ ሰንዳውንስ መካከል ቅድመ ስምምነት አድርገዋል። ይህም ማለት አቡበከር የክረምቱ የዝውውር መስኮት ሲከፈረት በቀጥታ አስፈላጊውን ህጋዊ የወረቀት ስራዎች ካከናወነ በኋላ ወደ ደቡብ አፍሪካው ክለብ የሚያደርገውን ዝውውር በይፋ የሚያጠናቅቅ ይሆናል። ስለዚህም በአሁኑ ሰዓት አቡበከር የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች ሲሆን ከክለቡም መልቀቂያ አልወሰድም። ቡናም አበቡበከር ከሰንዳውስ ጋር ቅድመ ስምምነት እንዲያደርግ ፍቃደኛ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል።
ይህን ተከትሎ ለኢትዮጵያ ቡና በቀጣይ ጨዋታዎች አገልግሎት የሚሰጠው አቡበከር ነገ በአስራ አንደኛ ሳምንት ከአዳማ ከተማ ጋር በሚኖረው ጨዋታ ይሰለፋል ወይ የሚለውን ለማወቅ ባደረግነው ማጣራት ተጫዋቹ ድሬዳዋ በማቅናት ቡድኑን እንዳልተቀላቀለ ያረጋገጥን ሲሆን የነገው ጨዋታ አልፎት ከ12ኛ ሳምንት ጀምሮ ለቡድኑ አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ሰምተናል።