[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
በኮስታሪካ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2022 ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ዓለም ዋንጫ አራተኛ ዙር ማጣርያ ታንዛኒያን 2ለ1 በመርታት ወደ መጨረሻው ዙር ማለፉን ያረጋገጠው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ ተጋጣሚውን ያወቀበት የጋና እና የዩጋንዳ ጨዋታ ዛሬ ተደርጓል፡፡
ዩጋንዳ ላይ በጋና 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቆ የነበረው ጨዋታ መልስ ዛሬ ተካሂዶ ጋና 5-0 ማሸነፍ ችላለች። ኤልቪን ባዱ በ22ኛው፣ ሳላማታ አብዱላይ በ26ኛው፣ ራህማ ጃፋሩ 82 እንዲሁም ዶሪስ ባድዋ በ88 እና 90+2ኛው ደቂቃ ለጋና ያስቆጠሩ ሲሆን በድምር ውጤት 7ለ1 አሸናፊ መሆን ችላለች።
ጋና በቀጣይ በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብሬኤል ከሚመራው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጋር የ180 ደቂቃ ፍልሚያ አድርገው አሸናፊው ቡድን ወደ ኮስታሪካው የዓለም ዋንጫ የሚያልፍ ይሆናል፡፡