በአምላክ ተሰማ የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታን ይመራል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ኢትዮጵያዊው ዳኛ በአምላክ ተሰማ ከስድስት ቀናት በኋላ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታን የሚመራ ይሆናል፡፡

የ2022 የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ ጨዋታዎች ከያዝነው ሳምንት ጀምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ክለቦች መካከል የሚደረግ ይሆናል፡፡ከስድስት ቀናት በኋላ በቀጣዩ ሳምንት ቅዳሜ ቀን 10፡00 ላይ የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታ የሆነው እና በሞሮኮው ራጃ ካዛብላንካ እና በደቡብ አፍሪካ አማዙሉ ክለብ መካከል በካዛብላንካ በሚገኘው ስታድ መሐመድ ስታዲየም የሚደረገውን ይህን ጨዋታ በካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ አስደናቂ አቋሙን ሲያሳይ የነበረው ኢትዮጵያዊው ዓለም አቀፍ ዳኛ በአምላክ ተሰማ በዋና ዳኝነት እንዲመራ ካፍ መድቦታል፡፡

ሱዳናዊው መሐመድ አብደላ እና ታንዛኒያዊው ፍራንክ ጆን በረዳትነት ሲመረጡ ሱዳናዊው መሐመድ አሊ መሐመድ በአራተኛ ዳኝነት የሚመሩ ይሆናል፡፡ካሜሩናዊው አሊ ኮናቴ ደግሞ ጨዋታውን በታዛቢነት እንደሚያገለግሉም ተያይዞ ተገልጿል፡፡