የአሰልጣኞች አስተያየት | አርባምንጭ ከተማ 1-1 ሲዳማ ቡና

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

በአቻ ውጤት ከተጠናቀቀው የዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ በኋላ ሶከር ኢትዮጵያ ከአሰልጣኞች ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርጋለች።

አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ – ሲዳማ ቡና

ስለ ጨዋታው

“ጥሩ ነው መጥፎ አይደለም። ግን የራሳችን ጨዋታ ነው የተበላሸብን። ያው እንግዲህ ኳስ ጨዋታ ማለት በኢንሲደንቶች የሚያጋጥሙ ነገሮችን መጠቀም ነው፡፡ በተደጋጋሚ እኛ ላይ ይሰጡ የነበሩ የቅጣት ምቶች እንዳይሰጡብን ጥንቃቄ ለማድረግ ሞክረናል ፤ ለልጆችም ነግረናል። ግን ያው እነዚህን ስህተቶች ስለፈፀምን ጎል አግብተውብናል። ከዛ በኋላ ግን የነበረው ጨዋታ ዝም ብሎ ጊዜ የመግደልን ሁኔታ ጨዋታውን ጠቅላላ አበላሽቶታል፡፡

ረጅም ሰዓት መርቶ ነጥቡን ስለማጣት

“በራሳችን ችግር ነው ፤ ጠንካራ ነው ማለት አይቻልም። ጥሩ ነው ቡድኑ ነገር ግን በቁጥጥር ስር ያደረግነው ጨዋታ ነውና የራሳችን ድክመት ነው የራሳችንን ጨዋታ አሳልፈን ሰጥተናል፡፡

በርከት ያሉ የአቻ ውጤቶች ስለመበራከታቸው

“አሁን ላይ እንደዛ ዓይነት ችግር የለም። አጋጣሚ በጨዋታ ሂደት ውስጥ በረጅም ጊዜ ጨዋታዎችን ስታደርግ ያጋጥማል አቻ ሊያጋጥምም ይችላል፡፡ ግን ከዛ በፊት የነበሩብን ችግሮች የውጤት ችግር በተፈጠሩበት ጊዜ ነበር አቻ የወጣነው። አሁን ግን ደህና ነው ምንም የሚያስከፋ አይደለም ከዚህ መውጣት እንዳለብን አስባለው፡፡

ስለ ቡድኑ ደስተኝነት

“ጥሩ ነው መጥፎ አይደለም እኮ። አሁን ባለፉት ሁለት ሦስት ጨዋታዎች አሁንም ዛሬ እውነት ለመናገር መሸነፍ አይደለም አቻ አይጠበቅብንም። አቻ እንወጣለን ብለንም አላሰብንም። ግን አቻ ወጥተናል ያው እንደ ስፖርት ቤተሰቡም እንደ አሰልጣኝም የምትቀበለው ነው፡፡

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ – አርባምንጭ ከተማ

ስለ ጨዋታው

“ጨዋታው እግዚአብሔር ይመስገን መልካም ነው፡፡ በመጀመሪያው አጋማሽ ኳሶችን መጫወት ችለዋል እነሱ ኳስን ተቆጣጥረውም ሲጫወቱ ነበር ተመችቷቸው ነበር፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ አርባምንጭ ግን ይሄን ነገር ነው የከለከልናቸው ፊትነሳችንንም ሞራላችንንም ከፍ አድርገን ገብተን ሁለተኛ አርባ አምስት ላይ ጥሩ ነበርን። ጨዋታውንም መጀመሪያ አጋማሽ ላይ እንደነበረ ብልጫ ሳይኖር እግዚአብሔርም ረድቶን አንድ ነጥብም አግኝተናል። ምክንያቱም የተወሰነ ሉዝ አድርገንም ስለመጣን ኢቺንም ማግኘቴ አንድ ነገር ነው። ከሸንፈት እንደመጣም ኢቺን ይዘህ ነገ ደግሞ ተስፋ ታደርጋለህ፡፡

ስለ ውጤቱ ተገቢነት

“አይ እነሱ የተሻለ የጎል ዕድል ፈጥረዋል እኔ በማግባት ነው የማምነው። ብልጫ እነሱ ከእኛ የተሻለ የጎል ዕድል ፈጥረዋል፡፡ ስለዚህ የእነርሱ ይሻላል፡፡”

ጎል የማስቆጠር ችግር ስለመኖሩ

“ይሄን እንቀርፋለን። የእኛ ችግር ብቻ አይመስለኝም። ምን አልባት አጠቃላይ ውድድሩ ላይ ምቹ ነገሮች አልነበሩም። ኮከብ ጎል አግቢ የነበረው በዘጠኝ ጨዋታዎች ላይ አራት ጎል ነው የተቆጠረው። ጨዋታዎችም ያልቁ የነበረው አንድ ለባዶ ወይም እኩል ለእኩል ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ከምን እንደሆነ በደንብ መመርመር ይፈልጋል፡፡ ዝም ብሎ እንደዚህ ነው ከማለት ያ ቢሆን ብዙ ጎሎችን ታያለህ ስለዚህ የሜዳ ስፋት የእኛም ድክመት ደግሞ እኛ የምንፈጥራቸው ስህተቶች ይኖራሉ፡፡ አንዱ ጎል እንዳይኖር ካደረገው በተለይ ሀዋሳ ሜዳ ላይ ማንኛውም ቡድን ቢውልድ አፕ ነው መሠረት የሚሆነው እሱን ማየት አልቻልንም። ለምን ሜዳው ምቹ አይደለም። ማንም ከሜዳው ቶሎ መውጣት ነው። አደጋ እንዳይፈጥር ለማጥቃት ምንጩ ላይ ችግር ስለነበረበት ያን ማየት አልቻልንም የኛ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ውድድሩ ላይ፡፡

ውጤት ስለመራቁ

“የውጤቱ በምንፈልገው ደረጃ እያመጣን አይደለም አንድ ነጥብም ጥሩ ነው፡፡ ተከታታይ ስታሸንፍ ላይ ትወጣለህ ከእኛ ጋር አብረው የነበሩ ወደ ላይ የወጡ አሉ። አንድ ስታሸንፍ አስራ አምስት ነው የምትገባው ሉዝ አድርገናል ምንፈልገውን ያህል እያመጣን አይደለም። ውጤታችን በቂ ነው የሚል ዕምነት የለኝም ደግሞ መስተካከል የሚችሉ ነገሮች የሚታዩ ነገሮች አሉ፡፡”