አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ወደ ሥራ ተመልሰዋል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ከቀናት በፊት ወልቂጤ ከተማን በፕሪምየር ሊጉ እየመሩ ህመም ገጥሟቸው የነበሩት አሰልጣኝ በዛሬው ዕለት ቡድናቸውን መደበኛ ልምምድ አሰርተዋል፡፡

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ11ኛው ሳምንት ጨዋታ እሁድ ዕለት ወልቂጤ ከተማ በመከላከያ 3ለ1 በተረታበት መርሀግብር ላይ የክለቡ አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ጨዋታው ሳይጋመስ ገና 10ኛው ደቂቃ ላይ ክለቡ መከላከያን እየመራ ባለበት ወቅት ህመም ገጥሟቸው በአፋጣኝ ወደ ሆስፒታል በአምቡላንስ ማምራታቸውን በወቅቱ ዘግበን እንደነበር ይታወሳል፡፡

አሰልጣኙን የታይፈስ እና ታይፎይድ ህመም አቅም አሳጥቷቸው መታመማቸው የሚታወስ ሲሆን ከሰሞኑ የህክምና ክትትላቸውን በማድረግ እና በጥሩ ጤንነት ላይ መገኘታቸውን ተከትሎ ሠራተኞቹ የፊታችን ቅዳሜ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለሚያደርጉት የ12ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ አሰልጣኙ በዛሬው ዕለት ልምምድ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 በማሰራት ወደ መደበኛ የስራ ገበታቸው መመለሳቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ አረጋግጣለች፡፡