ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ ቡድናቸውን ይመራሉ

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

በአፍሪካ ዋንጫው በካፍ የቴክኒካል ቡድን አባል በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

በካሜሩኑ የ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ ካፍ አሉኝ ከሚላቸው 24 ኤሊት ኢንስትራክተሮች መካከል አንዱ የነበሩት አብርሀም መብራቱ ከግብፁ የአፍሪካ ዋንጫ በመቀጠል ለሁለተኛ ጊዜ በካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የካፍ የቴክኒካል አባላት በመሆን እስከ አፍሪካ ዋንጫው ፍፃሜ ድረስ አገልግለዋል።

በአፍሪካ ዋንጫውን የቴክኒክ ሂደት ከአጋሮቻቸው ጋር ከገመገሙ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫን በመጨረሻው የፍፃሜ ጨዋታ ማግስት ሰጥተው የነበሩት ኢንስትራክተሩ በትላንትናው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። በመቀጠል በቀጥታ ወደ ድሬዳዋ አምርተው በዛሬው ዕለት ክለባቸውን የመጀመሪያ ልምምድን አሰርተዋል፡፡


ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች (ከሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ) በረዳት አሰልጣኙ አብረሀም መላኩ መሪነት የተጫወተው ባህርዳር ከተማ በ14 ነጥቦች 9ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ነገ ሐሙስ ምሽት 01፡00 ላይ በዋና አሰልጣኙ እየተመራ ሀዋሳ ከተማ ይገጥማል ፡፡