[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ፋሲል እና አዳማ ነጥብ ከተጋሩበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ አሰልጣኞች አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ – አዳማ ከተማ
ስለ ጨወታው እንቅስቃሴ
“ጥሩ ነው ከሞላ ጎደል ፋሲል ጠንካራ ቡድን ነው፡፡በተለይ በመጀመሪያው አጋማሽ በምንፈልገው መልኩ ተጫውተናል፡፡በሁለተኛው አጋማሽ ጎል ከማግባታችን ጋር ተያይዞ ትንሽ ወደ ኃላ ሸሽተናል ያ ደግሞ ለእነርሱ የመጫወቻ ሜዳ ማግኘት አስችሏል፡፡ ይሄ ተፈጥሯዊ ነው አንዳንድ ጊዜ ተጫዋቾች ያንን ለማስጠበቅ መሸሻቸው ያንን ለማስተካከል ሞክረናል በመጨረሻ አንድ ነጥብ አግኝተናል፡፡
ስለ ውጤቱ ተገቢነት
“ማሸነፍ ነበረብን ብዬ አስባለሁ። ጀማልም ቢሆን ይሄን ያህል በጣም የሚፈትን ሙከራዎችን አላስተናገደም። እንደውም የሚያስቆጭ የጎል ዕድሎችን አግኝተናል ብዬ አስባለሁ። ግን ከጠንካራ ቡድን ጋር እንደመጫወታችን አንድ ነጥብ ማግኘታችን መጥፎ አይደለም፡፡
ጎል ስለተቆጠረባቸው መንገድ
“ኖርማል ቀላል ኳስ ነው፡፡ ያው እግርኳስ በስህተት የታጀበ ነው ፤ ተጫዋቾች ይሳሳታሉ፡፡ተጫዋቾች ካልተሳሳቱ ጎል አይገባም። ግን እሱን አይደለም የምንፈልገው እንደ ቡድን በሁለተኛው አጋማሽ ምንድነው የተሳሳትነው ወደ ኋላ ሸሽተናል ያንን ጎል ካገባን በኋላ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ጎል አግብተን ጨዋታውን መጨረስ እንዳለብን ያስተምረናል፡፡”
ስለ አሜ መሀመድ
“እንግዲህ አሜ መሀመድ ያው ሜዳ ላይ ጠንክሮ ይሰራል። ባለፈው ሳምንታቶች ጎል ማግባት አልቻለም ፤ ይሄ ለሱም ለቡድናችንም ጥሩ ነው፡፡ ለምን ከፊት ያሉት ተጫዋቾቻችን ጎል ባገቡ ቁጥር ኮንፊደንሳቸው ከፍ ይላል ያ ደግሞ ለቡድናችን የሚያመጣው ነገር አለ፡፡”
አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ – ፋሲል ከነማ
ስለ ጨዋታው
“ጨዋታውን በሁለት ዓይነት መልኩ ባየው ጥሩ ነው። በመጀመሪያው አጋማሽ ብዙ የለቀቅናቸው ነገሮች አሉ። የኛ አማካዮችም ሆኑ ለማጥቃት የምንሄድበት መንገድ ሁሉ በተሻለ ዘግተውታል ፤ የነበረው መነሳሳትም ትንሽ አዳማ ጥሩ መልክ ነበረው፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ ሙሉ በሙሉ ያደረግነው ነገር በሙሉ ጥሩ ነው፡፡ የሚቻለንን ሁሉ ነው ያደረግነው። አርባ አምስት ደቂቃ ሙሉ እነሱ ጋር ውለናል ማለት ይቻላል፡፡ እንደምታየው ደግሞ እነሱም ጠቅላላ ከኋላ ነው ያሉት። ግን በተፈለገው ጥረት ለመሄድ ሞክረናል። የተሻለ አርባ አምስት ደቂቃ ፋሲል ነበረው ማለት እችላለሁ፡፡ በአጠቃላይ ውጤቱ በዚህ መልኩ ቢያልቅም የተሻለውን ነገር ፈጥረናል ብዬ አስባለው፡፡
የቆመ ኳስ ላይ ቡድንኑ ስለ ማዘውተሩ እና የፈጠራ ችግር ስለመኖሩ
“ክፍተቱ ሳይሆን ብዙ ክለቦች ላይ ስታየው ከኳስ ጀርባ የመጫወት ነገር አለ ያ አካባቢ በሙሉ ጥቅጥቅ ያ ስለሆነ ያንን እያወጣህ ነው የምትጫወተው ፈጣሪ ተጫዋቾች አሉ፡፡ግን በሚፈለገው መልክ አልተጠቀምንም ስፔስ ለማግኘተ ማለት ነው፡፡የቆመ ኳስ ማግኘት በራሱ አንድ ትልቅ ነገር ነው፡፡እሱ ላይ አጠቃቀማችን ደግሞ ለወደፊቱ ማሳደግ ይኖርብናል ብዬ አስባለው ለቀጣይ ጊዜያቶች በተለይ እንደኔ የማየው የመጀመሪያ አጋማሽ አጀማመራችን እንደ ሁለተኛው አጋማሽ አለመሆኑ ነው፡፡በመጀመሪያው አጋማሽ የምንለቃቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ሁለተኛው አጋማሽ ያለው መነሳሳት ቦታን ጠብቆ የመጫወት እስከ መጨረሻው የምናደርገው ሀይል ሁሉ መጀመሪያ አጋማሽ ላይ ማድረግ ቢያንስ ይሄ ነገር መስራት እንዳለብን ነው የሚሰማኝ፡፡
ስለ ያሬድ ባዬ በተጠባባቂ ሆኖ አለመሰለፉ እና የአምሳሉ የአየር ላይ ኳስ ችግር
“የአምሳሉ እንግዲ የታይሚንግ ጉዳይ ነው፡፡ከዚህ አይተን የሚመርበት ነገሮች አሉ፡፡ይሄ ነገር ዛሬ ላይ የበለጠ ያየሁበት ክፍተት እንጂ ብዙ ጊዜ ታይሚንጉም ጥሩ ነው፡፡ፕላስ ከሱ በፊት የሚረዱት የአጥቂ አማካዮች የማገዝ ባህሪ በመጀመሪያው አጋማሽ አይታይሞ እና አንዳንድ ጊዜ በሁለት ተጫዋቾች መሀል እየሆነ ትንሽ ውዥንብር የፈጠረበት ይመስለኛል፡፡የሚታይ እና የሚስተካከል ነው፡፡ያሬድ እንደሚታየው ከጉዳት ነው የመጣው ከሰበታ ጋር በነበረው ቡድን እንዳለ ነው ተከላካዩ ላይ ማንን ነቅለህ ማንን ነው የምታወጣው ስለዚህ ሰአት መጠበቅ አለበት እሱ ብቻ ሳይሆን ሌላ የፎርሜሽን ለውጥ ያደረግነው ለምሳሌ አሁን የመጨረሻዎቹ አምስት ስድስት ሰባት ደቂቃ ላይ በአራት መከላከል ትተን በሶስት ነው የተጫወትነው ኩሊባሊ ፣ ሳኛ እና አስቻለው እንዲቆመሙ ሌላው የበለጠ እንዲጫኑ ነው፡፡በዚህ በሶስት መከላከል ላይ የያሬድ አስተዋጽኦ ትልቅ ሊሆን ስለሚችል ይሄ ታክቲካል ፎርሜሽን እንደ ተጫዋቾቻችን ብቃት እንጠቀማለን ብዬ አስባለሁ፡፡
ስለ ዋንጫ ፉክክር
“ገና 20 ጨዋታ አለ 20 ጨዋታ አለ ሲባል እያንዳንዱን ጨዋታ መልቀቅ ሳይሆን ከዚህ ተምረን እንደገና መነሳት አለብን በቀጣይ እንግዲ ውጤት እያየን ነገ ነው አሁንም ከማንም የተሻለ የዋንጫ ተፎካካሪ እንደምንሆን እና መጨረሻውን በጥሩ ውጤት እንደመድማለን የሚለውን መንፈስ አሳድገን ነው እየሄድን ያለነው፡፡