​ድሬዳዋ ከተማ አሠልጣኝ ዘማርያም ላይ ውሳኔ አሳልፏል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

በቅርቡ ለዋና አሰልጣኙ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ጥሪ ያስተላለፈው ድሬደዋ ከተማ አዲስ ውሳኔ ማስተላለፉ ታውቋል።

በቅርቡ ባቀረብነው ዘገባ ድሬዳዋ ከተማ ለአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ በላከው ደብዳቤ ከአሰልጣኙ ጋር ያለውን ጉዳይ በህግ የማጣራት ሂደቱ እንዳለ ገልፆ  በጊዜያዊነት ውሳኔ ሊያስተላልፍ መሆኑ ተከትሎ ከአሰልጣኙ ጋር ለመነጋገር በዛሬው ዕለት ቀጠሮ መያዙን ገልፀን ነበር።

በጥሪው መሰረትም አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ የክለቡ ፅህፈት ቤት መገኘታቸው ታውቋል። በክለቡ በኩል ተወክለው ከተገኙ አመራሮች ጋር በነበራቸው ቆይታ ክለቡ ያስተላለፈው ውሳኔ ምን እንደሆነ በደብዳቤ ተገልፆላቸዋል። በውሳኔው መሠረትም አሠልጣኙ ከ20 ዓመት በታች ቡድኑን ዝቅ ብለው እንዲያሰለጥኑ መደረጉን እና ከዛሬ ጀምሮ በስራ ገበታቸው እንዲገኙ ትዕዛዝ ተላልፏል።

አሰልጣኝ ዘማርያም በበኩላቸው በቀጣይ ስለሚሆነው ነገር ከጠበቆቻቸው ጋር ተማክረው ምላሻቸውን አደንደሚያሳውቁ ገልፀው ደብዳቤውን ተቀብለው ወጥተዋል።