አዲሱ የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋናቲኖ ነገ አአ ይገባሉ

የአለምአቀፉ የእግርኳስ አስተዳዳሪ አካል /ፊፋ/ ፕሬዘዳንት በመሆን ባለፈው ወር ወደ ስልጣን የመጡት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ነገ ምሽት አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡

የ45 አመቱ ስዊዝ/ጣልያናዊ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት በፌዴሬሽኑ ጋባዥነት ሲሆን በኢትዮጵያ በሚያደርጉት ቆይታም ከፌዴሬሽኑ ሃላፊዎች ጋር የሚያደርጉትን ውይይት ጨምሮ የፌዴሬሽኑን ፅህፈት ቤት እንዲሁም እንደ የኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ እና ፊፋ ጎል ፕሮጀክት የመሳስሉ የእግርኳስ ማዕከላትን የሚጎበኙ ይሆናል፡፡

በጉዳዩ ላይ ለሶከር ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁነይዲ ባሻ ጉብኝቱ በኢትዮጵያ እና በፊፋ መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት እንደሚያጠናክር ተናግረዋል፡፡ “አዲሱ ፕሬዝዳንት በስልጣን ዘመናቸው መጀመርያ ለጉብኝት መምጣታቸው በሁለታችን መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር ነው፡፡ በእግርኳስ ልማት ላይ ልንሰራ ያሰብናቸው ነገሮችን ወደፊት እንድንገፋበት ያደርጋል”ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *