ለኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን የተመረጡ ተጫዋቾች ቁጥር ከ50 በላይ ሆኗል

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ለ2017 የዛምቢያ ከ20 አመት በታች ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት አሰልጣኝ ግርማ ሀብተዮሃንስ እና ረዳቶቹ ሲሳይ አብርም እና ፀጋዘአብ አስገዶምን በመመደብ ባለፈው ሳምንት ወደ ዝግጅት ቢገባም በየእለቱ ለቡድኑ የሚጠሩ ተጫዋቾች መብዛት ለአሰልጣኞቹ ስራ አዳጋች እየሆነ መምጣቱ ታውቋል፡፡

PicsArt_1458669944161

ከ20 አመት በታች ቡድኑ ባለፈው ሳምንት 38 ተጫዋቾችን በመምረጥ ዝግጅት ቢጀምርም በእድሜ እና ከተስፋ ቡድን ተጫዋቾች ባለመመረጣቸው ምክንያት ጥያቄ በማጫሩ ከ20 በላይ ተጨማሪ ተጫዋቾች በጊዜያዊ ስብስብ ውስጥ ተካተዋል፡፡ በምርጫው ላይ ክለቦች ተጫዋቾቻቸው እንዲመረጡ ጥያቄ በማቅረብ ቡድኑ በተጫዋቾች ብዛት እንዲጨናነቅ እንዳደረጉት ለሶከር ኢትዮጵያ የደረሳት መረጃ ያመለክታል፡፡

PicsArt_1458669776388

በአሁኑ ሰአት ከ20 አመት በታች ቡድኑ ከከፍተና ሊግ ፣ ከፕሪሚየር ሊግ ፣ ከክልል ክለቦች እና ከተስፋ ሊግ የተውጣጡ ከ50 ተጫዋቾች በላይ በመያዙ የአሰልጣኝ ቡድኑ የመጨረሻዎቹን 25 ተጫዋቾች ለመምረጥ እርስ በእርስ ማጫወትን መርጧል፡፡ ትላንት እና ዛሬ ቡድኑን 4 ቦታ በመክፈል እያንዳንዱ ጨዋታን ለ45 ደቂቃዎች በማድረግ ተጫዋቾችን ለመለየት ጥረት የተደረገ ሲሆን የከፍተኛ ሊግ ጨዋታ አድርገው የተመለሱ ተጫዋቾችን ያካተተ የምርጫ ጨዋታ ዛሬ ተደርጓል፡፡ በምርጫ ጨዋታው አማካኝነት 18 ተጫዋቾች ትላንት የተቀነሱ ሲሆን በነገው እለት ተጨማሪ 13 ተጫዋቾች ተቀንሰው የመጨረሻዎቹ 25 ተጫዋቾች ይታወቃሉ ተብሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *