​የአሰልጣኞች አስተያየት | ወልቂጤ ከተማ 0-4 ቅዱስ ጊዮርጊስ

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልቂጤ ከተማን ከረታበት ጨዋታ በኋላ የቡድኖቹ አሰልጣኞች ሀሳባቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ አጋርተዋል። 

አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው – ወልቂጤ ከተማ

ስለጨዋታው

“ያው እንደተመለከታችሁት ነው። በቀይ የወጣ ተጫዋች ነበር። ሳምንቱን መሉ እኛ ጥሩ አልነበርንም። በላዬ ላይ ሰው መጥቷል እየተባለ ሲወራ ነበር። እንደውም ይሄ ነገር ጥሩ ነው ብዬ እገምታለሁ ፤ እንደዚህ አይደረግም። በዚህ አጋጣሚ ግን ለወልቂጤ ደጋፊ ፣ ለወልቂጤ ህዝብ ወደ ፕሪምየር ሊግ ስገባ ከጎኔ ለነበሩት ሁሉ ምስጋና አቀርባለሁ።”

አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ስለጨዋታው

“የምንፈልገው እና የሰራናቸው ስራዎች ነበሩ። ያንንም ተጫዋቾቼ በአግባቡ በመተግበራቸው በጣም ደስ ብሎኛል ፤ ኮርቼባቸዋለው።

በሁለተኛው አጋማሽ ስለመቀዛቀዛቸው

“አንደኛ የፀሀይ ነው የምንጫወተው ፤ የዘጠኝ ሰዓት ጨዋታ ነው። ጉልበታችንን ሙሉ ለሙሉ መጨረስ የለብንም። ባገኘነው አጋጣሚ እና የእነሱ አንድ ተጫዋች በቀይ ወጥቷል ከዛም በመነሳት ማግኘት የሚገባንን ተነጋግረን ነበር። ከዛ በመነሳት መጨረሻ አካባቢ ጎሎች አግብተን 4-0 አሸንፍናል።

ድሬዳዋ ከመጡ ጀምሮ በበድኑ ስላለው ለውጥ

“የማሸነፍ ፍላጎታችን እና የአንድነታችን ጥንካሬ ነው። ወደፊትም በዚሁ አኳኋን ነው የምንሄደው።

ጊዮርጊስ ወደ አስፈሪነቱ ስለመመለሱ

“የተሻለ ነገር ለመስራት አቅሙ ያላቸው ብዙ ተጫዋቾች አሉ ፤ ያንን ከሰራንበት የበለጠ ውጤት እንደሚያመጡ እናውቃለን። አሁን ትኩረታችን እዛ ላይ ነው።”

ያጋሩ