ዋልያዎቹ ብሊዳ ከተማ ገብተዋል

ጋቦን ለምታስተናግደው የ2017 አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በምድብ 10 የአልጄሪያ ብሄራዊ ቡድንን ብሊዳ ላይ የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሃራዊ ቡድን ከ19 ሰዓት ጉዞ በኃላ አልጀርስ ገብቷል፡፡ ዋልያዎቹ ከአልጄሪያ ርዕሰ መዲና በደቡብ ምዕራብ 45 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ወደ ምትገኘው ብሊዳ ከተማ በየብስ ትራንሸፖርት ተጉዘዋል፡፡

28 ልዑካን ቡድን የያዘው ብሄራዊ ቡድኑ ሰኞ ምሽት 4፡45 ጉዞውን ወደ አልጀርስ ሲጀምር ለስምንት ሰዓታት በካይሮ ትራንዚት ማሳለፍ ተገዷል፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ ገነ ጨዋታውን በሚያደርግበት 37ሺህ ተመልካች መያዝ አቅም ባለው ስታደ ምስጠፋ ቻክር የመጀመሪያ ልምምዱን የሚያደርግ ይሆናል፡፡ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ እና አማካዩ ጋቶች ፓኖም ብሄራዊ ቡድኑ አልጀርስ ዓይር ማረፊያ በደረሰበት ወቅት ከአልጄሪያው የእግርኳስ ቴሌቪዥን ቻናል ኤል ሄድዳፍ ጋር ስለአልጄሪያ ቡድን እና ታዋቂ ተጫዋቾቻቸው ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *