[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከጋና ጋር ላለበት ወሳኝ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ለ27 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርቧል።
በኮስታሪካ አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የዓለም የሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ሁለት የአህጉራችን ብሔራዊ ቡድኖች ቦታ እንዳላቸው ይታወቃል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም የሁለተኛ፣ ሦስተኛ እና አራተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎችን አሸንፎ በመጨረሻ ዙር ከጋና አቻው ጋር ወሳኝ ግጥሚያ ይቀረዋል። የጋና ብሔራዊ ቡድንም መጋቢት 3 በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከሁለት ሳምንት በኋላ ደግሞ መጋቢት 17 በኬፕ ኮስት ስታዲየም ለሚደረጉት የደርሶ መልስ ጨዋታ ከቀናት በፊት ዝግጅቱን የጀመረ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ከነገ በስትያ ዝግጅቱን እንደሚጀምር ተገልጿል።
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው ዘገባም የቡድኑ አሠልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ከስር የተዘረዘሩትን 27 ተጫዋቾች እንደጠሩ ያመላክታል።
ከአዲስ አበባ ከተማ፡ አርያት ኦዶንግ፣ ማክዳ ዓሊ
ከአዳማ ከተማ፡ እየሩሳሌም ሎራቶ፣ ናርዶስ ጌትነት
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡ ብዙዓየሁ ታደሰ፣ ትዕግስት ኃይሌ፣ አረጋሽ ካልሳ
ከድሬዳዋ ከተማ፡ ብርቄ አማረ፣ ከባህር ዳር ከተማ፣ ባንቺአየሁ ደመላሽ
ከኢትዮ ኤሌክትሪክ፡ ኝቦኝ የን፣ መስከረም ኢሳይያስ፣ ገነት ኤርሚያስ፣ ቤቲ ዘውዱ
ከመከላከያ፡ መዓድን ሣህሉ፣ ነፃነት ፀጋዬ፣ ገነት ኃይሉ፣ ቤተልሔም በቀለ፣ እፀገነት ግርማ፣ ዓይናለም አደራ፣ መሳይ ተመስገን
ከሀዋሳ ከተማ፡ ቱሪስት ለማ፣ ረድኤት አስረሳኸኝ፣ ቅድስት ቴቃ
ከቦሌ ክፍለ ከተማ፡ ንግስት በቀለ
ከአሰላ ከተማ፡ ለቱ ግርማ
ከፋሲል ከነማ፡ የሺ አስመቸ
ከን/ላ/ክ/ከተማ፡ ሕይወት አመንቴ
ተጫዋቾቹ ሰኞ የካቲት 7 በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ቤት ረፋድ 4፡00 ላይ ሪፖርት እንዲያደርጉም ተጠቁሟል።