[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ሰላሳ አምስት ቡድኖችን በሦስት ምድቦች አቅፎ የሚደረገው የ2014 የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎች የሚጀምርበት ቀን ታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ስር ከሚካሄዱ ውድድሮች መሀል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የ2014 የውድድር ዘመን የመጀመሪያው ዙር ጨዋታዎች በሶስት ምድቦች ተከፍሎ በወላይታ ሶዶ ፣ ቡራዩ እና አሰላ ከተማ ከታህሳስ 8 እስከ ጥር 23 ድረስ ሲደረግ የቆየ ሲሆን የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎች ደግሞ የሚደረጉበትን ከተማ እና የሚደረግበትን ቀን ፌዴሬሽኑ አሳውቋል፡፡
በዚህም መሠረት የካቲት 19 ዙሩ እንዲጀመር ሲወሰን ቡሌ ሁራ ከተማን መሪ በማድረግ የተጠናቀቀው ምድብ ሀ በቢሾፍቱ ከተማ ፣ በጂንካ ከተማ መሪነት የመጀመሪያው ዙር የተጠናቀቀው ምድብ ለ በወልቂጤ ከተማ እና አረካ ከተማን በአንፃሩ በመሪነት አድርጎ ተገባዶ የነበረው ምድብ ሐ በአሰላ ከተማ እንዲደረግ ፌዴሬሽኑ ለክለቦች በላከው ደብዳቤ ጠቁሟል፡፡