የ20 ዓመት በታች ውድድሩ ተራዝሟል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ባሳለፍነው ሳምንት የዕጣ ማውጣት ሥነስርዓት የተከናወነለት ውድድር መጀመሪያ ላይ ለውጥ ተደርጓል።

የ2014 የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ታዳጊ ወጣቶች ፕሪምየር ሊግ በ19 ክለቦች መካከል እንደሚካሄድ ይጠበቃል። ውድድሩ በሁለት ምድብ ተከፍሎ ምድብ ሀ በጎንደር ምድብ ለ ደግሞ በአሰላ እንደሚደረግ ባሳለፍነው ሳምንት በጁፒተር ሆቴል በተከናወነው የዕጣ ማውጣት ሥነስርዓት ላይ መወሰኑም አይዘነጋም።

በመጀመሪያ እንደነበረው ውጥን ይህ ውድድር ከየካቲት 12 ጀምሮ በሁለቱ ከተሞች እንደሚካሄድ እየተጠበቀ የነበረ ቢሆንም ዛሬ ፌዴሬሽኑ ባሳወቀው መሰረት ግን ቀኑ ለውጥ ተደርጎበታል። በዚህም መሰረት የተወሰኑ ክለቦች MRI ምርመራ በመጨረስ ውል ያላጠናቀቁ በመሆናቸው ሳቢያ የውድድሩ የመጀመሪያ ቀን ወደ የካቲት 19 ተገፍቷል። ለውድድሩ መራዘም ምክንያት ከሆነው ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘም ፌዴሬሽኑ ክለቦች እስከ የካቲት 15 ድረስ ውላቸውን እንዲያጠናቅቁ አሳስቧል።

ያጋሩ