​የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጥሪ አድርጓል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

አሰልጣኝ እንዳልካቸው ጫካ የሚመራው ብሔራዊ ቡድን ለመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታው ተጫዋቾችን መጥራቱን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

በ2022 በህንድ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ለማለፍ የመጀመርያ ዙር ማጣርያ ውድድር ያለበት የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የጌዴኦ ዲላው አሰልጣኝ እንዳልካቸው ጫካን  መሾሙን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ለዝግጅት 44 ተጫዋቾች ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

ብሔራዊ ቡድን ከዩጋንዳ አቻው ጋር የካቲት 25 ከሜዳ ውጪ መጋቢት 11 ደግሞ በሜዳው ግጥሚያውን ሲያደርግ ለጨዋታው ለተከታዮቹ ተጨዋቾች ጥሪ አድርጓል። ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ነገ 8፡00 በካፍ ልህቀት ማዕከል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉም ጥሪ ተላልፏል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጥሪ የተደረገላቸውን 44 ተጫዋቾች እንደሚከተለው ይፋ አድርጓል