መልካሙ ፍራውንዶርፍ ለሀኖቨር 96 ፈርሟል

ከሊቨርፑል ጋር የተለያየው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ወደ ጀርመን ተመልሷል።

ከውድድር ዓመቱ መጠናቀቅ በኋላ ከቀዮቹ ጋር የአራት ዓመት ቆይታውን አጠናቆ ክለብ አልባ ሆኖ የቆየው የ20 ዓመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ መልካሙ ፍራውንዶርፍ የሃኖቨርን ከሀያ ሦስት ዓመት በታች ቡድን ለመቀላቀል ወደ ጀርመን ተመልሷል። አማካዩ በ2020 ከጀርመኑ ሆፈንሃይም መርሲሳይድ ደርሶ ሁለት የዋናው ቡድን ጨዋታዎችን ማድረግ ቢችልም እድገቱ እንደተጠበቀው መሆን አልቻለም፤ ይህንን ተከትሎም ለአዲስ ፈተና ወደ ጀመርን ተመልሷል።


ተጫዋቹ የእንግሊዙን ክለብ ለቆ ሀኖቨር 96ን ከተቀላቀለ በኋላም በግል የማህበራዊ ትስስር ገፁ በስሜት የተሞላ የስንብት መልእክት አጋርቷል። “በሀኖቨር 96 እግር ኳስ ክለብ ወደ አዲስ ምዕራፍ እየገባሁ ነው፤ ዛሬም በሊቨርፑል አካዳሚ ያሳለፍኳቸውን አራት አስደናቂ ዓመታትን የምሰናበትበትና የማመሰግንበት ቀን ነው፤ አመሰግናለሁ” ብሏል።