​የፕሪምየር ሊጉ ቀጣይ የውድድር ከተማ ታውቋል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከሁለተኛ ዙር ጅማሮ አንስቶ የሚካሄድበት ከተማ ታውቋል።

የ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ጅማሮውን በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በማድረግ 9 ሳምንታትን ካከናወነ በኋላ ከብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በኋላ በሀገራችን የምስራቁ ክፍል በድሬዳዋ እየተከናወነ ይገኛል። ሊጉ ቀድሞ በተያዘለት እቅድ መሰረት እስከ መጀመሪያው ዙር መገባደጃ (15ኛ ሳምንት) ድረስ በድሬዳዋ ከተከናወነ በኋላም በሌሎች ከተሞች ይደረጋል ተብሎ ሲጠበቅ ቢቆይም ከሰሞኑን የሦስት ሳምንት ጨዋታዎች በድሬዳዋ ሊቀጥሉ ይችላሉ የሚሉ ወሬዎች በርክተው ነበር።

የሊጉ የበላይ አስተዳዳሪ አካልም ዛሬ ረፋድ በጉዳዩ ዙርያ ስብሰባ ካከናወነ በኋላ ከ16ኛ ሳምንት ጀምሮ ሊጉ በአዳማ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም እንዲደረግ መወሰኑን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች። ከእረፍት በኋላም ሊጉ የሚጀመርበትን ቀን አክሲዮን ማኅበሩ በቀጣይ ይፋ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።

ማስታወሻ፡ ከላይ የተጠቀምነው ምስል ከወራት በፊት የተነሳ መሆኑን እንገልፃለን

 

ያጋሩ