ኢትዮጵያዊው የመስመር ተጫዋች ለአል ሜሪክ ቤንቲዩ ፊርማውን አኑሯል።
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከወልቂጤ ከተማ ጋር ያሳለፈው የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ፋሲል ከነማ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የመስመር ተጫዋች ራምኬል ሎክ ወደ ደቡብ ሱዳኑ አልሜሪክ ቤንቲዩ አቅንቷል። የተጠናቀቀው የውድድር ዓመት የደቡብ ሱዳን ሊግ አሸናፊ በመሆን በምስራቅና እና የመካከለኛው አፍሪካ ክለቦች ዋንጫ ሀገሩን ወክሎ ለመሳተፍ ወደ ስፍራው ያቀናው ክለቡ ኢትዮጵያዊውን የመስመር ተጫዋች በአንድ ዓመት ውል የግሉን አድርጓል።
በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በክለብ ደረጃ ደግሞ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ካነሳበት ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨምሮ ለበርካታ ክለቦች ከተጫወተ በኋላ በዛሬው ዕለት ለደቡብ ሱዳኑ ክለብ ፌርማውን ያኖረው ራምኬል ሎክ በሴካፋ ክለቦች ዋንጫ ለመሳተፍ ወደ ስፍራው አቅንቶ ስብስቡን ተቀላቅሏል።