በኦሬንጅ ካፍ ኮንፌድሬሽንስ ካፕ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች ተደርገው ሁለተኛውን ዙር የተቀላቀሉ ክለቦች ታውቀዋል፡፡ ልክ እንደቻምፒየንስ ሊጉ ሁሉ የሰሜን አፍሪካ ክለቦች በውድድሩ ላይ የበላይነታቸውን ማሳየታቸውንም ቀጥለዋል፡፡
የታንዛኒያው አዛም የደቡብ አፍሪካውን ቤዴቬስት ዊትስን ዳሬሰላም ላይ 4-3 በማሸነፍ ሁለተኛውን ዙር ተቀላቅሏል፡፡ በአይስ ክሬም አምራች ድርጅት ስር ለሚተዳደረው አዛም ሶስቱን ግቦች ኮትዲቯሪያዊው ኪፕሬ ቲቼቲቼ አስቆጥሮ ሐት-ትሪክ ሲሰራ ቀሪዋን አንድ ግብ ታንዛንያዊው ጆን ቦኮ ከመረብ አዋህዷል፡፡ ለጆሃንስበርጉ ክለብ አብድናጎ ሞሲትላጋ ፣ ጃቢላኒ ሶንግዊ እና ናሚቢያዊው ሄሬሪኮ ቦቴስ በስማቸው አስመዝግበዋል፡፡ የጋናው ሚዲአማ በአባስ መሃመድ ሁለት ግቦች ታግዞ የሊቢያውን አል ኢቲሃድ ከውድድር ውጪ አድርጓል፡፡ ኢትዮጵያዊው አማካይ አዲስ ህንፃ ክለብ የሆነው የሱዳኑ አልሃሊ ሸንዲ ደግሞ የዲ.ሪ. ኮንጎው ሴንት ኢሎኢ ሉፖፖን በኬሌቺ ኦሶንዋ ግብ ታግዞ 1-0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል፡፡
የናይጄሪያው ናሳራዋ ዩናይትድ በአልጄሪያው ሲኤስ ኮንታስንታይን 4-1 በሆነ ሰፊ ውጤት ተሸንፎ ከኮንፌድሬሽንስ ካፕ ውጪ ሆኗል፡፡ ከሳምንት በፊት ናሳራዋ ኮንስታንታይን 1-0 ያሸነፈ ሲሆን የመልሱ ጨዋታ ሊጠናቀቅ 13 ደቂቃዎች እስኪቀሩት ድረስ ሁለቱ ቡድኖች 1-1 ነበሩ፡፡ ለኮንስታንታይን የድል ግቦቹን አምበሉ ያሲን ቤዛዝ በፍፁም ቅጣት ምት፣ አህመድ ሚሳአይዳ፣ ሙራድ ሜግሃኒ እንዲሁም ማዳካስካራዊው ፖሊን ቮቪ በጨዋታ አስቆጥረዋል፡፡ ለተሸናፊው ደግሞ ናሳራዋ ባቱሬ ያሮ ኳስ እና መረብን አገኛኝቷል፡፡ የኮንጎ ብዛራዛቪሉ ቪ ክለብ ሞካንዴ፣ የሞሮኮው ካውካብ ማራካሽ፣ የአንጎላው ሳግራዳ ኤስፔራንስ፣ የቱኒዚያው ኤስፔራንስ፣ የግብፃቹ ምስር አል ማቃሳ እና ኢኤንፒፒአይ እንዲሁም የአልጀሪያው መውሊዲያ ኦራን ሁለተኛው ዙር ተቀላቀሉ ሌሎች ክለቦች ናቸው፡፡
የመጀመሪያ ዙር ውጤቶች
ሲኤስ ኮንስታንታይን (አልጄሪያ) 4-1 ናሳራዋ ዩናይትድ (ናይጄሪያ) [4-2]
አዛም (ታንዛኒያ) 4-3 ቤድቬስት ዊትስ (ደቡብ አፍሪካ) [7-3]
ፖሊስ (ሩዋንዳ) 0-1 ቪ ክለብ ሞካንዴ (ኮንጎ ብራዛቪል) [0-1]
ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ (ቱኒዚያ) 5-0 ሬኔሳንስ (ቻድ) [7-0]
ዶን ቦስኮ (ዲ.ሪ ኮንጎ) 1-0 ምስር አል ማቃሳ (ግብፅ) [2-3]
ሊጋ ማፑቶ (ሞዛምቢክ) 0-0 ሳግራዳ ኤስፔራንስ (አንጎላ) [0-1]
ኤስሲ ጋግኖአ (ኮትዲቯር) 2-2 ኤምሲ ኦራን (አልጄሪያ) [2-4]
ኤፍዩኤስ ራባት (ሞሮኮ) 2-1 ዩኤምኤስ ደ ሎም (ካሜሮን) [3-2]
ባራክ ያንግ ኮንትሮለርስ (ላይቤሪያ) 2-0 ካውካብ አትሌቲክ ክለብ ማራካሽ (ሞሮኮ) [2-3]
ጄኬዩ ኤፍሲ (ዛንዚባር) 0-1 ስፖርተ ክለብ ቪላ (ዩጋንዳ) [0-5]
ሲኤፍ ሞናና (ጋቦን) 3-0 አትሌቲኮ ኦሎምፒክ (ብሩንዲ) [5-0]
ዛናኮ (ዛምቢያ) 3-1 ሃራሬ ሲቲ (ዚምባቡዌ) [5-2]
ኢኤንፒፒአይ (ግብፅ) 4-1 አፍሪካ ስፖርትስ ዲ አቢጃን (ኮትዲቯር) [6-1]
ኤኤስ ካሉም (ጊኒ) 0-0 ስታደ ጋቢሲየን (ቱኒዚያ) [1-2]
አልሃሊ ሸንዲ (ሱዳን) 1-0 ሴንት ኢሎኢ ሉፖፖ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) [2-2]
ሚደአማ (ጋና) 2-0 አል ኢቲሃድ (ሊቢያ) [2-1]
የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች
ኤስፔራንስ ደ ቱኒዝ (ቱኒዚያ) ከ አዛም (ታንዛኒያ)
ስታደ ጋቢሲየን (ቱኒዚያ) ከ ዛናኮ (ዛምቢያ)
ኤፍዩኤስ ራባት (ሞሮኮ) ከ ስፖርት ክለብ ቪላ (ዩጋንዳ)
ቪ ክለብ ሞካንዴ (ኮንጎ ብራዛቪል) ከ ሳግራዳ ኤስፔራንስ (አንጎላ)
መውሊዲያ ኦራን (አልጄሪያ) ከ ካውካብ አትሌቲክ ክለብ ማራካሽ (ሞሮኮ)
ሲኤፍ ሞናና (ጋቦን) ከ ኢኤንፒፒአይ (ግብፅ)
ሲኤፍ ኮንስታንታይን (አልጄሪያ) ከ ምስር አል ማቃሳ (ግብፅ)
አልሃሊ ሸንዲ (ሱዳን) ከ ሚደአማ (ጋና)