ወጣቱ የመስመር አጥቂ ከአዳማ ከተማ ጋር ተለያይቷል

ቀሪ የውል ጊዜ የቀረው ዮሴፍ ታረቀኝ ከአዳማ ከተማ ጋር መለያየቱ እርግጥ ሆኗል።

ከታዳጊ ቡድን አንስቶ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ ከአዳማ ከተማ ጋር ያለፉትን አመስት ዓመታት አብሮ መዝለቅ የቻለው ዮሴፍ ታረቀኝ ከክለቡ ጋር መለያየቱ ታውቋል።

የመስመር አጥቂው ከአዳማ ከተማ ጋር ቀሪ የአንድ ዓመት ውል ቢኖረውም የሁለት ወር ደማወዝ ያልተከፈለው መሆኑን ተከትሎ የመልቀቂያ ደብዳቤ ፌዴሬሽኑ እንዲሰጠው ያቀረበውን ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ ዛሬ ፌዴሬሽኑ መልቀቂያውን እንደሰጠው አውቀናል።

ከታዳጊ ቡድን አንስቶ ወደፊት ተስፋ እንደሚጣልበት የተገመተው ዮሴፍ ታረቀኝ ከ2015 አጋማሽ ጀምሮ ወደ ዋናው ቡድን በማደግ በግሉ ጥሩ የውድድር ጊዜ እያሳለፈ የሚገኝ ሲሆን በዘንድሮው የውድድር ዓመት አስራ ሁለት ጎሎችን ማስቆጠሩ ይታወቃል።

ዮሴፍ በቀጣይ ማረፊያው የሀገር ውስጥ ክለብ ወይስ ወደ ውጭ ይጓዛል የሚለውን ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።