አበባየሁ ሀጂሶ አዲስ ክለብ ተቀላቅሏል

ያለፉትን ስድስት ዓመታት በወላይታ ድቻ ቤት ቆይታ ያደረገው አበባየሁ ሀጂሶ ወደ ሌላ ክለብ አምርቷል።

በወላይታ ዲቻ ከ17 ዓመት በታች ቡድን አንስቶ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ ማገልገል የቻለው እና ከወላይታ ድቻ ማልያ ውጭ ለብሶ የማያቀው አማካዩ አበባየሁ ሀጂሶ ለሁለት ዓመት ውል ወደ አዲስ ክለብ ማቅናቱ እርግጥ ሆኗል።

አበባየሁ የተቀላቀለው ክለብ ሲዳማ ቡና መሆኑ ሲታወቅ ዛሬ የህክምና ምርመራውን አድርጎ ቡድኑን በይፋ መቀላቀሉን አውቀናል። በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ለሚመራው ሲዳማ ቡና የመጀመርያ ፈራሚ የሆነው አበባየሁ ከዚህ ቀደም ከአሰልጣኙ ጋር በጦና ንቦቹ ቤት አብሮ መስራቱ ይታወሳል።

አማካዩ ባለፉት ዓመታት በግሉ ካሳየው ጥሩ እንቅስቃሴ አንፃር በቀጣይ ለሲዳማ ቡና መልካም አገልግሎትን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ሲዳማ ቡና በቀጣዮቹ ቀናት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው እንደሚቀላቅሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።