[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
የቢሾፍቱ ከተማ የመሐል ተከላካይ በመኪና አደጋ ህይወቱ አለፈ፡፡
በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ምድብ ሐ ተሳታፊ በሆነው ቢሾፍቱ ከተማ በመሐል ተከላካይነት ሲጫወት የሚታወቀው ኖህ ደሳለኝ ወይም ሳንቾ በድንገተኛ አደጋ ህይወቱ አልፏል፡፡ ኖህ በትውልድ ከተማው ቢሾፍቱ ከተማ ከ2004 ጀምሮ ለተከታታይ አራት ዓመታት ከተጫወተ በኋላ ወደ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ በመዘዋወር የአንድ አመት ቆይታን በማድረግ በድጋሚ 2010 እስከ ዘንድሮው የውድድር ዓመት ድረስ በድጋሚ ወደ ቢሾፍቱ ከተማ ተመልሶ እየተጫወተ ይገኝ ነበር፡፡ 1984 የተወለደው ይህ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ትናንት ዕሁድ ምሽት በትውልድ ሀገሩ ቢሾፍቱ በባለ ሦስት እግር መኪና (ባጃጅ) ተሳፍሮ ሲጓዝ ልዩ ስሙ ዝቋላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰው ግጭት ተጫዋቹ በተወለደ በ30 ዓመቱ ህይወቱ አልፏል፡፡
በዛሬው ዕለት ረፋድ ላይ በቢሾፍቱ አቦ ቤተክርስቲያ ስርአተ ቀብሩ የተፈፀመ ሲሆን ሶከር ኢትዮጵያም ለቤተሰቦቹ ፣ ለወዳጆቹ እና ለተጫዋቹ አድናቂዎች የተሰማንትን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀች መፅናናትን ትመኛለች፡፡