ቢንያም ፍቅሬ በግብፅ የሚያደርገውን ዝውውር መስመር ለማሲያዝ ካይሮ ገብቷል

የወላይታ ድቻው ወጣት አጥቂ ቢንያም ፍቅሬ በግብፅ ክለቦች ተፈልጎ ካይሮ እንደሚገኝ ታውቋል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ ተስፋ ሰጪ የሆነ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ በሊጉ ላይ ከደመቁ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው የወላይታ ድቻው አጥቂ ቢኒያም ፍቅሬ ትላንት ወደ ካይሮ ማምራቱ ታውቋል። በአሁኑ ወቅት በግብፅ ክለቦች የሚያደርገውን ዝውውር መስመር ለሚያሲያዝ ካይሮ እንዲሄድ ካመቻቸለት ከወኪሉ አዛርያስ ተስፋፂሆን ጋር አብሮ የሚገኘው ቢንያም ሁለት ክለቦች እርሱን ለመውሰድ ፍላጎት ማሳየታቸውን ወኪሉ ነግሮናል።

የመጀመርያው ፈላጊ ክለብ እስማኤሊያ ሲሆን ቢንያምን ያለ ምንም ሙከራ በሚደረጉ ድርድሮች በቀጥታ ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተሰምቷል። ሁለተኛው ክለብ ደግሞ አል ኢታሀድ ሲሆን ይህ ክለብ ደግሞ የሙከራ ጊዜ ሰጥቶ ቢንያምን ለመውሰድ እንዳሰበ ተነግሮናል።

አጠቃላይ የቢንያም ማረፊያ የትኛው ክለብ የሚለውን ከነገ ጀምሮ በሚደረጉ ድርድሮች የሚወሰን መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።