[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
በአሠልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመራው ጅማ አባጅፋር በዛሬው ዕለት ለሦስት ተጫዋቾች የእግድ ደብዳቤ እንደሰጠ ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።
የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ክለብ የሆነው ጅማ አባጅፋር የሊጉን ዋንጫ ከፍ ባደረገ ማግስት በየዓመቱ ላለመውረድ የሚጣጣር ቡድን እንደሆነ ይታወቃል። የትግራይ ክልል ክለቦች አለመሳተፋቸውን ተከትሎ የእነርሱን ቦታ ለማግኘት በተደረገው ውድድር ዳግም በሊጉ የመቆየት ዕድል አግኝቶ ዘንድሮ በሊጉ እየተሳተፈ የሚገኘው ቡድኑም በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ወደ ስብስቡ ከቀላቀላቸው ተጫዋቾች መካከል ሦስቱን በዛሬው ዕለት ማገዱ ታውቋል።
ድረ-ገፃችን ባገኘችው መረጃ መሠረት የግብ ዘቡ ዮሐንስ በዛብህ እንዲሁም የመስመር ተጫዋቾቹ አስናቀ ሞገስ እና ሚኪያስ ግርማ ከዲሲፕሊን ጋር በተያያዘ ለጊዜው እግድ ተላልፎባቸዋል። ክለቡ ሦስቱን ተጫዋቾች ዛሬ ቢያግድም ባሳለፍነው ሳምንት እና ዛሬ በድምሩ ለ10 ተጫዋቾች የመጀመሪያ እና ሁለተኛ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደሰጠ አውቀናል።