የወልቂጤ ከተማ እና የሲዳማ ቡናን ጨዋታ የመሩት ረዳት ዳኛ ከውድድሩ ተሰናብተዋል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ባሳለፍነው ሳምንት የተደረገውን የወልቂጤ ከተማ እና የሲዳማ ቡናን ጨዋታ ከመሩት ዳኞች መሐል አንዱ የቅጣት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡

በዘንድሮ የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ላይ እየታዩ ካሉ ክፍተቶች መካከል በተለየ መልኩ ረዳት ዳኞች የሚፈፅሙት ተደጋጋሚ የውሳኔ አሰጣጥ ክፍተት በጉልህ ይነሳል፡፡ በተጠናቀቀው የ13ኛ ሳምንት የፕሪምየር ሊጉ መርሐ-ግብር ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ተገናኝተው ያለ ጎል አቻ መለያየታቸው ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ በዕለቱ ወልቂጤ ከተማ በመጀመሪያ አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአማካዩ በሀይሉ ተሻገር አማካኝነት ግብ አስቆጥሮ የነበረ ቢሆንም በጨዋታው በክቡር ትሪቡን በኩል በረዳት ዳኝነት ተሰይመው ጨዋታውን የመሩት እና ረጅም ዓመታትን በፌዴራል ረዳት ዳኝነት ያገለገሉት ዳንኤል ጥበቡ ግቧ ከጨዋታ ውጪ ነች በማለት ሽረው ነበር። ረዳት ዳኛው ግቧን በመሻራቸው የዳኞች ኮሚቴ ጉዳዩን ከገመገመ በኋላ ዳኛውን ከውድድሩ በማገድ ከድሬዳዋ አሰናብቷቸዋል፡፡

በቀሩት የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ ጥፋት የሚፈፅሙ ዳኞች ተመሳሳይ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ይጠበቃል፡፡