[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
በእግድ ሰንብተው በድጋሚ ወደ ክለቡ እንዲመለሱ ተደረገው የነበሩት አሰልጣኝ ዳንኤል ገብረማርያም የልቀቁኝ ደብዳቤን አስገብተዋል፡፡
በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ካደረጋቸው አስራ አራት ጨዋታዎች በአንዱ ብቻ ድል ያደረገው ሰበታ ከተማ ዋና አሰልጣኙ፣ ረዳት አሰልጣኞቹን እና የቴክኒክ ዳይሬክተሩን ከስብስቡ ማገዱ ይታወሳል፡፡ ይሁን እና የክለቡ የበላይ አካላት ከሳምንታት በፊት ካገዷቸው ረዳቶች መካከል ዳንኤል ገብረማርያም እና ብርሀን ደበሌ ወደ ክለቡ ተመልሰው ስራቸውን እንዲጀምሩ የሚል ትዕዛዝ አስተላልፎ የነበረ ቢሆንም አሰልጣኝ ብርሀን ደበሌ በአስራ አራተኛው ሳምንት መርሐ-ግብር ከባህር ዳር ጋር 1ለ1 የተጠናቀቀውን ጨዋታ በብቸኛ አሰልጣኝነት መርተዋል።
ከጨዋታው ቀደም ብሎ ግን ወደ ክለቡ እንዲመለሱ ከተባሉት መካከል አሰልጣኝ ዳንኤል ገብረማርያም “እኔን ያመጣኝ ዋና አሰልጣኙ ዘላለም ሽፈራው ነው። በክለቡ የተለያዩ ችግሮች ስላሉ አልሰራም።” በማለት አቋማቸውን ማሳወቃቸው የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ በይፋዊ መንገድ ከክለቡ ጋር ላለመቀጠል መወሰናቸውን ገልፀው የሁለት ገፅ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች፡፡
አሠልጣኙ ያስገቡት ደብዳቤ ክለቡ እንደደረሰው ያወቅን ሲሆን የቦርድ አመራሮቹም ጥያቄው በራሳቸው በኩል ስለመጣ እንደሚያፀድቁ ተጠቁሟል።
ከክለቡ ጋር የሦስት ዓመት ውል የነበራቸው አሰልጣኙ ያስገቡት ደብዳቤ ከታች ተያይዟል 👇👇👇