ቻምፒዮንስ ሊግ ፡ ሃይለየሱስ ባዘዘው የኢንያምባ እና ቪታሎን ጨዋታ ይመራል

የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የ1ኛ ዙር የመልስ ጨዋታዎች በነገ እና ከነገ በስቲያ ሲደረጉ የቡሩንዲው ቪታሎ እጅግ ጠባብ የማለፍ ተስፋ ይዞ የናይጄርያው ኢንያምባን ነገ ያስተናግዳል፡፡ የ2007 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ዳኛ ተብሎ የተመረጠው ሃይለየሱስ ባዘዘው ጨዋታውን እንዲመራ በካፍ ተሹሟል፡፡ የሃይለየሱስ ረዳት በመሆን ጨዋታውን የሚመሩት ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የ2007 የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ረዳት ዳኛ ሃይለራጉኤል ወልዳይ እና ክንፈ ይልማ በረዳት ዳኝነት ተመድበዋል፡፡ ዘካርያስ ግርማ ደግሞ 4ኛ ዳኛ በመሆን ጨዋታውን ይመራሉ፡፡

የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ የመልስ ጨዋታ ፕሮግራሞች የሚከተሉት ናቸው፡- (በቅንፍ የተቀመጠው የመጀመርያ ጨዋታ ውጤቶች ናቸው)

ቅዳሜ መጋቢት 10 ቀን 2008

ኤሲ ሊዮፖርድስ (ኮንጎ ብራዛቪል) ከ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ) (0-2)

ኤል ሜሪክ (ሱዳን) ከ ዋሪ ዎልቭስ (ናይጂሪያ) (1-0)

ያንጋ አፍሪካ (ታንዛኒያ) ከ ኤፒአር (ሩዋንዳ) (2-1)

ቪታሎ (ቡሩንዲ) ከ ኤኒየምባ (ናይጄሪያ) (1-5)

ኤቷል ደ ሳህል (ቱኒዚያ) ከ ኦሲ ኮሪብጋ (ሞሮኮ) (1-1)

አል አሃሊ (ግብፅ) ከ ሬክሬቲቮ ዱ ሊቦሎ (አንጎላ) (0-0)

ዛማሌክ (ግብፅ) ከ ዩኒየን ዱዋላ (ካሜሮን) (1-0)

ሲኤንኤፒኤስ (ማዳጋስካር) ከ ዋይዳድ ካዛብላንካ (ሞሮኮ) (1-5)

 

እሁድ መጋቢት 11 ቀን 2008

አል ሂላል (ሱዳን) ከ አል አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) (0-1)

ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኢትዮጵያ) (2-2)

አሴክ ሚሞሳ (ኮትዲቯር) ከ ካይዘር ቼፍስ (ደቡብ አፍሪካ) (1-0)

ኢኤስ ሴቲፍ (አልጄሪያ) ከ ኤቷል ዲ ኮንጎ (ኮንጎ ብራዛቪል) (1-1)

ፌሮቫያሮ (ሞዛምቢክ) ከ ኤስ ቪታ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) (0-1)

ኮተን ስፖርት (ካሜሮን) ከ ስታደ ማሊያን (ማሊ) (0-2)

ኤምኦ ቤጃ (አልጄሪያ) ከ ክለብ አፍሪካ (ቱኒዚያ) (0-1)

ሆሮያ (ጊኒ) ከ ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ) (1-4)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *