የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን የመጀመርያ ልምምዱን ዛሬ አድርጓል

በ2017 በዛምቢያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ከ20 አት በታች የአፍሪካ ዋንቻ ለማለፍ በቅድመ ማጣርያው የሶማልያ ብሄራዊ ቡድንን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን የመጀመርያ ልምምዱን ዛሬ ረፋድ በአዲስ አበባ ስታድየም አድርጓል፡፡

በአሰልጣኝ ግርማ ሀብተዮሃንስ እና ረዳቶቻቸው ሲሳይ አብርሃም እና ፀጋዘዓብ አስገዶም የሚመራው ከ20 አመት በታች ቡድኑ በዚህ ሳምንት መጀመርያ 38 ተጫዋቾችን ያሳወቀ ሲሆን በዛሬው ልምምድ ላይ 22 ተጫዋቾች ልምምዳቸውን ሰርተዋል፡፡ ለሁለት ተከፍሎ መጫወትም የልምምዳቸው አካል ነበር፡፡ በልምምዱ ላይ ከከፍተኛ ሊግ የተመረጡት አመዛኞቹ ተጫዋቾች ከክለባቸው ጋር ለጨዋታ ወደተለያዩ የክልል ከተሞች በማምራታቸው ያልተገኙ ሲሆን ከወላይታ ድቻ የተመረጡ 4 ተጫዋቾችም ነገ በኢትዮጵያ ሊግ ዋንጫ ከመከላከያ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ምክንያት አልተገኙም፡፡

በእድሜ ጉዳይ እና ከተስፋ ቡድኖች በርካታ ተጫዋቾ ባለመመረጣቸው መነጋገርያ የሆነው ከ20 አመት በታች ቡድኑ በቀጣዩ ሳምንት የስብስቡን ቁጥር ወደ 23 ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አመዛኞቹን ተጫዋቾች ከከፍተኛ ሊግ በመምረጣቸው ምክንያትም ጨዋታው እየተቃረበ ሲመጣ ከፍተኛ ሊጉ ሊቋረጥ ይችላል ተብሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *