[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ከእግር ኳስ መሰረታዊ አካላት መካከል አካል ብቃት አንዱ ነው። በተለይም በእግር ኳስ ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ በቻሉት ሀገራት ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራበት እንመለከታለን። በሀገራችን ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ በተለያዩ ጊዜያት ጥያቄዎች ሲነሱ ቆይተዋል። ይህንን ነገር ይዘን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአካል ብቃት አሰልጣኝ የሆኑት ዶ/ር ዘሩ በቀለን አናግረናል።
* የአካል ብቃት ጥቅም እንዴት ይገለፃል?
አካል ብቃት የዘመናዊ ስፖርት ስልጠና አንዱ አካል (pillar) ነው። እኛ ብዙ ጊዜ ከሜዳ እንቅስቃሴ ጋር እናገናኘዋለን ነገር ግን ዋናው ዓላማው ተጫዋችን ከጉዳት ለመከላከል ነው።
የጡንቻ ፣ የአተነፋፈስ እና የልብ ብቃትን እንደዚሁ ለማጎልበት ይጠቅማል። ከሰውነት ውስጥ አላስፈላጊ ንጥረነገሮች እንዲወገዱ እና የሰውነት አካላቶቻችን በአግባቡ ስራቸውን ማከናወን እንዲችሉ ይረዳል።
አካል ብቃት ጥሩ ሲሆን ስነ ልቦናም ጠንካራ ይሆናል። ተጫዋች ተጠናክሮ እንዲጫወት ያስችለዋል። ነገሮችን ማድረግ እንደሚችል ያስባል። ሌሎች የቴክኒክ ጉዳዮችንም እንዲያሻሽል ይረዳል። ታክቲካዊ ነገሮችንም ለመተገበር ያግዛል። ለምሳሌ በመልሶ መከላከል ለመጫወት ፍጥነት ያስፈልጋል። ይህን ማምጣት የሚቻለው በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ነው።
የአካል ብቃት እንቅሰቃሴ 5 መሰረታዊ ነገሮችን በውስጡ አቅፎ ይዟል። እነዚህም:
1) endurance,
2) strength,
3) power
4) agility
5) speed ናቸው።
በአጠቃላይም major soccer fitness በመባል ይታወቃሉ።
* በክለብ እና በብሄራዊ ቡድን መካከል ያለው ልዩነት
በክለብ አላማህን በአመቱ ከፋፈልህ ታስቀምጣለህ። Strength የሚሰራው በክለብ ደረጃ ነው እንጂ በብሄራዊ ቡድን አይሰራም። ምክንያቱም ተጫዋቾቹ ከተለያየ አይነት አሰለጣጠን ነው ወደዚህ አይነት ጨዋታ የሚመጡት። ይህ ከሌለ ደግሞ power ላይ መስራት አይቻልም። ከዛ ውጭ ያላቸውን ፍጥነት እና endurance እንዳያጡ ይሰራል። የኛ ልጆች strength ላይ ክፍተት አለባቸው። ነገር ግን ሁሉም ማለት አይደለም።
High intensity running ላይ የኛ ልጆች ጥሩ ናቸው። ይህ ካካለልከው ሜዳ ወደ 5% ያለውን በhigh intensity running ትሮጣለህ። ለምሳሌ በቡርኪና ፋሶ ጨዋታ ላይ ልጆቹ የነበራቸውን ፍጥነት መመልከት ይቻላል። በ10 ቀን ልዩነት ያደረጉት ሶስተኛ ጨዋታቸው ነበር ነገር ግን የነበራቸው ፍጥነት ጥሩ የሚባል ነበር።
* በአካል ብቃት ብልጫ የሚወሰድብን ምክንያት
ሌሎች የአፍሪካ ቡድኖች የኛን ደካማ እንቅስቃሴ ይመርጣሉ። ለምሳሌ ኳስ ሲሻገር ያለውን ሁኔታ መመልከት ይቻላል።
በዘር (genetics) እና ከልምምድ ባህልም አንጻር ጠንካራ ናቸው። አካል ብቃት ላይ ትኩረት አድርገው ይሰራሉ ምክንያቱም መጫወት የሚፈልጉት በታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች ነው።
* የእኛ ቡድን አካል ብቃት ችግር ተፈጥሮ ወይስ ስላልተሰራበት ?
በአካል ብቃት ጠንካራ የሆኑ ተጫዋቾች አሉ። ነገር ግን ከቴክኒክ ወይም ታክቲክ አንፃር የሚጎድላቸው ነገር እንዳለ እናስተውላለን። ከአመጋገብ ጋር balance አድርጎ ልምምድን አለመስጠት ክፍተትም አለ። ሁለገብ የሆነ የእግር ኳስ አተገባበር አለመኖሩ አንዱ ችግር ነው።
ትናንሽ ሰውነት ለመንቀሳቀስ ብዙ ኃይልን አይጠይቅም። ስለዚህ የኛ ተጫዋቾች ከሌሎች አፍሪካውያን አንፃር ፍጥነት አላቸው።
ዶ/ር ዘሩ በቀለ ስፋት እንዳስረዱት በተጫዋቾችን ጋር የተመጣጠነ እና ተፈጥሯዊ ሁኔታን ያገናዘበ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ውጤታማ ያደርጋል።
ክለቦች ለአካል ብቃት የሚሰጡትን ትኩረት መጨመር አለባቸው። ዶ/ር ዘሩ እንደተናገሩትም ለልምምድ ሜዳ እንደሚሰጠው ትኩረት ሁሉ ለጅምናዚየም እና ለአካል ብቃት አሰልጣኝ ቦታ መስጠት ያስፈልጋል። ሀገራችን ሆነ ተጫዋቾቻችን በትላልቅ መድረኮች ስኬታማ መሆን እንዲችሉ አካል ብቃት በአግባቡ መሰራት አለበት።