የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ፡ ሽመልስ በቀለ ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በተከታታይ በቀጣዩ ሳምንት አርብ እና ማክሰኞ ከአልጄርያ ጋር ለሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ዝግጅቱን እደረገ የሚገኘው ስብስብን ለመቀላቀል ሽመልስ በቀለ ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

የፔትሮጄቱ አማካይ በአሰልጣኝ ዮሃንስ ጥሪ ከተደረገላቸው 24 ተጫዋቾች መካከል አንዱ ሲሆን ከክለቡ ቶሎ በመለቀቁ ዋልያዎቹን በጊዜ የመቀላል እድል አግኝቷል፡፡ በነገው እትም ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር ልምዱን ማድረግ ይጀምራል፡፡ እንደ ሽመልስ ሁሉ ጌታነህ ከበደ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ ቢጠበቅም ይህን ዘገባ እስካጠናከርንበት ሰአት ድረስ እንዳልመጣ ታውቋል፡፡ በቅርብ ሳምታት በመልካም አቋም ላይ የሚገኘው የዩኒቨርሲቲ ኦፍ ፕሪቶርያ አጥቂ ጌታነህ ከበደ ነገ አዲስ አበባ በመግባት ዋልያዎቹን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *