ሮበርት ኦዶንካራ እና አይዛክ ኢዜንዴ ለዩጋንዳ ብሄራዊ ብድን ተጠርተዋል

የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች የሆኑት ግብ ጠባቂው ሮበርት ኦዶንካራ እና የመሃል ተከላካዩ አይዛክ ኤዜንዴ ጋቦን ለምታስተናግደው የ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዪጋንዳ በምድብ 4 ከቢርኪናፋሶ ጋር ለምታደርጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ጥሪ ተደርጎላቸዋል፡፡

የክሬንሶቹ አሰልጣኝ ሰርቢያዊው ሰርጂዮቪች ሚሉቲን የ2015 የሴካፋ ዋንጫን ብሄራዊ ቡድኑ እንዲያሸንፍ ቁልፍ ሚና የነበራቸውን ፋሩክ ሚያ፣ ሴዛር ኡኩቲ፣ ጆሴፍ ኦቻያ እንዲሁም ኢሪሳ ሲኪሳምቡ ጨምረው ጠርተዋል፡፡ በደቡብ አፍሪካ አብሳ ፕሪምርሺፕ ድንቅ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘው የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ የአሁኑ የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ግብ ጠባቂ ዴኒስ ኦኒያንጎ፣ ጆፍሪ ማሳ እና ኤማኑኤል ኦኩዊ ሚቾ ለቢርኪናፋሶው ጨዋታ እንዲረዷቸው ከመረጣቸው ተጫዋቾች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

IMG_0110

አይዛክ እና ሮበርት በህዳር ወር ዩጋንዳ ቶጎን በአለም ዋንጫ ማጣሪያ 4-0 ስታሸንፍ የብሄራዊ ቡድኑ ስብስበ ውስጥ የነበሩ ሲሆን አይዛክ ሁለቱንም ጨዋታዎች በቋሚነት መጫወት ችሏል፡፡ ምድብ 4ን በስድስት ነጥብ የምትመራው ዩጋንዳ ከ1978 እ.ኤ.አ በኃላ ለመጀመሪያ ግዜ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለመመለስ ጠንካራ ስራዎችን በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡ ቦትስዋና እና ቡርኪናፋሶ በሶስት ነጥብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሲሆን ሁለት ጨዋታዎችን የተሸነፈችው ኮሞሮስ የምድቡ ግርጌ ላይ ትገኛለች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *