የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድ ከሶማልያ ጋር ለሚያደርገው የአፍሪካ ከ20 አመት በታች ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ዝግጅት ለ38 ተጫዋቾችን መርጧል፡፡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለ20 አመት በታች ቡድኑ የሙገሩ አሰልጣኝ ግርማ ሀብተዮሃንስን ዋና አሰልጣኝ ፣ የሰበታ ከተማው ረዳት አሰልጣኝ ሲሳይን ረዳት አሰልጣኝ የደደቢቱን ፀጋዘአብ አስገዶም ደግሞ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ አደርጎ የሾመ ሲሆን ለ38 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ነገ ዝግጅቱን ይጀምራል፡፡ በምርጫው ላይ አመዛኞቹ ተጫዋቾች ከከፍተኛ ሊጉ ክለቦች የተመረጡ ሲሆን በቻን ጊዜያዊ ስብስብ ውስጥ ተካትቶ የነበረው የአዳማ ከተማው ቡልቻ ሹራ ፣ የኢትዮጵያ ቡናው እያሱ ታምሩ ፣ የኤሌክትሪኩ አሰግድ አክሊሉ እንዲሁም የወላይታ ድቻው ፈቱዲን ከፕሪሚር ሊጉ ከተመረጡ ተጫዋቾ መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ የተመረጡት ተጫዋቾች ዛሬ ሪፖርት የሚያደርጉ ሲሆን በሳምንቱ መጨረሻ በሚደረጉት የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች ምክንያት ከአዲስ አበባ ውጪ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ክለቦች ውስጥ የሚገኙ ተጫዋቾች ሪፖርት ማድረግ የማይችሉ በመሆናቸው ከጨዋታዎች ሲመለሱ ሪፖርት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በአሰልጣኝ ግርማ ሀብተዮሃንስ ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾ የሚከተሉት ናቸው፡-
ግብ ጠባቂዎች
አሰግድ አክሊሉ – ኤሌክትሪክ
ተክለማርያም ሻንቆ – አአ ከተማ
ሰሚር ነስሮ – አዳማ ከተማ (ተስፋ ቡድን)
በሽር ደሊል – ሙገር ሲሚንቶ
ተከላካዮች
ስንታየሁ መንግስቱ – ወላይታ ድቻ
ፈቱዲን ጀማል -ወላይታ ድቻ
ዳንኤል ራህመቶ – አአ ፖሊስ
ተስፋዬ ሽብሩ – አአፖሊስ
ዳግም ንጉሴ – ወላይታ ድቻ
ያሲን ጀማል – አአ ዩኒቨርሲቲ
እንየው ካሳሁን – አአ ከተማ
ሚልዮን ብሬ – አአ ከተማ
ሳሙኤል በለጠ – ወሎ ኮምቦልቻ
ሀይደር ሙጣፋ – ጅማ አባ ቡና
አስናቀ ሞገስ – ባህርዳር ከተማ
አማካዮች
ሱራፌል ጌታቸው – ሙገር ሲሚንቶ
ሱራፌል አወል – ጅማ አባ ቡና
በሱፍቃድ ነጋሽ – መቐለ ከተማ
ተሾመ መንግስቱ – አዳማ ከተማ
አዲስ ግርማ – አዳማ ከተማ
መርዋን ራያ – ሙገር ሲሚንቶ
ቢንያም ትዕዛዙ – ኢትዮጵያ መድን
ዳዊት ተፈራ – ጅማ አባ ቡና
እያሱ ታምሩ – ኢትዮጵያ ቡና
ዘሪሁን ብርሃኑ – አአ ዩኒቨርሲቲ
ከነአን ማርክነህ – አአ ዩኒቨርሲቲ
ተመስገን ተስፋዬ – አአ ዮኒቨርሲቲ
ደስታ ደሙ – ሙገር ሲሚንቶ
አንዱአለም ፍቃዱ – ሙገር ሲሚንቶ
ምስጋና ወልደዮሃንስ – ደቡብ ፖሊስ
አጥቂዎች
ሮቤል ጥላሁን – ቡራዬ ከተማ
አለምሰገድ ዘንደቦ – አአ ፖሊስ
ቡልቻ ሹራ – አዳማ ከተማ (ቢጫ ቴሴራ)
አሜ መሃመድ – ጅማ አባ ቡና
ሙሉቀን ታሪኩ – ፋሲል ከተማ
አብዱራህማን ሙባረክ – ፋሲል ከተማ
ያሬድ ዳዊት – ወላይታ ድቻ
ጂብሪል መሃመድ – አዳማ ከተማ (ቢጫ ቴሴራ)
ፎቶ – አሰልጣኝ ግርማ ሐብተዮሃንስ ጥሪ የተደረገለቸው ተጫዋቾች ረፖርት ማድረጋቸውን ሲያረጋግጡ