[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ሱፐር ስፖርት በሲዳማ ቡና አሸናፊነት ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኋላ ከአሠልጣኝ የድህረ-ጨዋታ ሀሳብ ተቀብሏል።
ገብረመድህን ኃይሌ – ሲዳማ ቡና
ጨዋታው እንዴት ነበር?
ጥሩ ነበር። ወደ እረፍት ስንሄድ ሦስት ነጥብ ይዘን ብንሄድ ለሁለተኛው ዙር ጥሩ ስንቅ ነው የሚሆነን። በጣምም አስፈላጊ ነው። በመጀመሪያዎቹ ጨዋታዎች ጥሩ ሳንሆን ከዛ በኋላ እያሻሻልን እዚህ ደረጃ መድረሳችን ትልቅ ነገር ነው። ድሬዳዋ ከገባን ጀምሮ ጥሩ የሚባል ነገር ነው ያገኘው። አልተሸነፍንም። አራት አሸንፎ ሁለት አቻ መውጣት ራሱ ትልቅ ነገር ነው። የፈለግነውን ነገር ለማግኘት ዛሬ የተሟላ ሊያደርገው ይችላል። ዕድሉንም አግኝተናል። ጥሩ ነው።
እየተመሩ በእረፍት ሰዓት ስላስረካከሉት ነገር?
የነበረብንን ክፍተቶች አንስተን እነሱን ለማረም ጥረት አድርገናል። ሁል ጊዜ በተቀደምክ ቁጥር ለማስተካከል መሄድ አስፈላጊ አይደለም። ጥሩም አይሆንም። መቀደምም የለብህም። ከዛ በኋላ ደግሞ ከተቀደምክ በኋላ በምን መልኩ ማስተካከል አለብህ በሚለው ነገ ትንሽ መቆጣጠርን እና እይታን ይፈልጋል። እይታህ ጥሩ ከሆነ የተበላሸውን አስተካክለህ ለውጤት ትዳረጋለህ።
የመጀመሪያው ዙር ብቃታቸው?
ሁለት ገፅታ አለው። የመጀመሪያዎቹ 6 እና 7 ጨዋታዎች ለእኛ ጥሩ የሚባሉ አልነበሩም። ከዛ በኋላ በተለይ ወደ መጨረሻው አካባቢ ሀዋሳ ላይ እና ድሬዳዋ ባደረግናቸው ስድስት ጨዋታዎች በጣም ጥሩ ሊባል የሚችል ጊዜ አሳልፈናል። በአጠቃላይ ድሬዳዋ ጥሩ ጊዜ ያሳለፍንበት ነው።
ሙሉጌታ ምህረት – ሀዲያ ሆሳዕና
እየመሩ ውጤት ስላጡበት ምክንያት?
ትልቁ ችግራችን ጥንቃቄ ነው። በራሳችን ጥንቃቄ ጉድለት እንጂ እነርሱ በራሳቸው ያደረጉት አይደለም። ጥንቃቄ ነው። ሌላ የተለየ ነገር የለውም።
ስላደረጉት እንቅስቃሴ?
ከእረፍት በፊት ወደፊት እየሄድን ነበር የምንጫወተው። ከእረፍት በኋላ ግን ሌላ መጨመር ነበር ሀሳባችን። ግን ታክቲካሊ ቦታችን ላይ ባለመገኘታችን ባገኙት አጋጣሚ ሁለተኛውን ጎል አግብተዋል። እንጂ የተለየ ነገር ምንም የለውም።
በሁለተኛው ዙር ውድድር ስለሚያደርጉት መሻሻል?
ማሻሻያዎች ይኖራሉ። እኛ ጋርም የሚቀሩ ነገሮች ስላሉ ሰርተን እንመጣለን። በተጫዋቾችም ጭምር በሁለተኛው ዙር ተዘጋጅተን መምጣት አለብን። ተጫዋቾቼ በአጠቃላይ ጥሩ ናቸው። የሚቀሩን ነገሮች ስላሉ እነሱን አሟልተን እንመጣለን።