የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ መግለጫ ሰጥተዋል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

👉”ረጅም ዓመት በሴቶች ላይ ቆይቻለው። ምን መደረግ እንዳለበት በደንብ አውቃለሁ”

👉”ዋና ዓለማው ለዋናው እና ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ግብዓት የሚሆኑ ተጫዋቾችን ማውጣት እና ማፍራት ነው”

👉”ፌዴሬሽኑ ከፍተኛ ትኩረት ነው የሰጠው” 

በህንድ አስተናጋጅነት በሚደረገው የዓለም የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የአፍሪካ ዞን የማጣሪያ መርሐ-ግብር ከሰሞኑ ሲጀመሩ ከዮጋንዳ አቻው ጋር የሚፋለመው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንም አሰልጣኝ እንዳልካቸው ጫካን በዋና አሰልጣኝነት የመረጠ ሲሆን አሠልጣኙም ለጨዋታው ቡድናቸው እያደረገ የሚገኘውን ዝግጅት አስመልክቶ ወሎ ሰፈር በሚገኘው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት መግለጫ ሰጥተዋል። አሠልጣኙም ተከታዩን አጠር ያለ ሀሳብ በስፍራው ለተገኙ የብዙሃን መገናኛ አባላት አጋርተዋል።

“ለተጫዋቹች ጥሪ ያደረግነው የካቲት 11 ነበር። ለ44 ተጫዋች ነበር ጥሪ ያደረግ። ከዛም እነዚህን ተጫዋቾች ወደ ማጣራት ነው የሄድነው። ይህ ያደረግነው 25 ተጨዋቾችን መምረጥ ስላለብን የሁለት ቀን ጨዋታዎችን አዘጋጅተን ነበር። በነዛ ሁለት ቀናት ተጫዋቾችን አይተን ለኢትዮጽያ ብሔራዊ ቡድን ይመጥናሉ የምንላቸውን 25 ተጫዋቾች ይዘን ከየካቲት 14 ጀምረን እስካሁን ድረስ ዝግጅት ላይ ነን።” ብለዋል። ከአሠልጣኙ አጭር ሀሳብ በኋላ ጋዜጠኞች ጥያቄዎችን አቅርበው ምላሽ መሰጠት ተጀምሯል።

ስለውድድሩ እና ስላላቸው ልምድ..?

ወደ ብሔራዊ ቡድን ስመጣ ረጅም አመት በሴቶች ላይ ቆይቻለው። ምን መደረግ እንዳለበት በደንብ አቃለሁ። ዋና ዓላማው ለ20 ዓመት በታች እና ለዋናው ብሔራዊ ቡድን የሚሆኑ ተጫዋቾችን ማብቃት እና ማዘጋጀት ነው። ተጫዋቾችን እንዴት ማብቃት እንዳለብኝ ስስራ ነበር። አሁን ላይ ላለው ብሔራዊ ቡድን የሚጫወቱ ልጆች እንዴት እንደሰራው ስለማቅ ምናልባት እነሱንም ከ17 አመት በታች ጌዜ ተሰጥቶ በቆይታ ብዙ እሰራለሁ ብዬ አስባለሁ። ዋና አለማው ግን ብሔራዊ ቡድኑን ለዋናው እና ከ20 በታች ግብዓት የሚሆኑ ልጆችን ማውጣት እና ማፍራት ነው።

ስለተጋጣሚ ቡድን?

ተጋጣሚ ቡድን ከባድ ቡድን ነው። ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ። እነሱም ያው እንደኛው ሴቶች ናቸው። እንዴት ማሸነፍ እንዳለብን ተጫዋቾቹ ላይ የአሸናፊነት መንፈስ ሞልተን ቡድኑ አሸናፊ የሚሆንበትን መንገድ እንቀይሳለን። እኔ ከየትኛውም ቡድን ስንጫወት እንዴት ተጫዋቾቹን ማውጣት እና አሸናፊ መሆን እንዳለብን ትኩረት አድርጌ እሰራለው። የተጋጣሚ ቡድናችን አጨዋወት ለማየት ከረዳቶቼ ጋር ሆኜ ሞክረናል። ምን አይነት ጨዋታ እንደሚጫወቱ እየተመለከትን ነበር። የ2012 ከ17 አመት በታች የነበረው ከኛ ቡድን የነበሩትን እንዴት እንደሚጫወቱ አሁንም 2022 የያዙትን ቡድን ለማየት ሙክረናል። በምን አይነት መልኩ መዘጋጀት እንዳለብን ራሳችንን በጥቂት ቀናት ውስጥ ስናዘጋጅ ነበር።

ስለቅጥር ሁኔታ…?

የቅጥር ሁኔታን በተመለከተ የመጀመሪያ ትኩረት ያደረግነው ለዚህኛው ጨዋታ ነው። ይህንን ጨዋታ እንዴት መወጣት እንዳለብን ነው የምናስበው። ከዛ በኋላ ከፌዴሬሽኑ ጋር እንነጋገራለን። ይህን አመት ይህንን ጊዜ የተባባልነው ነገር የለም። ግን የረጅም ጊዜ እቅድ እንዳላቸው ተነግሮኛል። እነሱም ያንን ያደርጋሉ ብዬ አስባለሁ። በእድሜ ጉዳይ አነስ የሚሉ ተጫዋቾች ታሳቢ አድርገን ነው የመረጥነው። ምክንያቱ ደሞ ከ17 አመት በታች የሚል ውድድር ስለሌለ ልንመርጥ የምንችለው ከአካዳሚዎች እና ውድድር ላይ ካሉት ነው። ፌዴሬሽኑን ማመስገን እፈልጋለሁ። ፌዴሬሽኑ ከስር ለመስራት ቁርጠኝነት አሳይቷል። ትኩረት በመስጠት ተደርጎ በማያቅ ረዳት ሆኖ በሚሰሩ አራት አሰልጣኞች እንድምመርጥ አድርጎኛል። አንድ የበረኛ እንዲሁም ሁለት ረዳት አሰልጣኝ ናቸው። እነሱም በጣም ይረዱኛል። አሰልጣኞቹ ብዙ ጊዜ ሴቶች ላይ የሰሩ ናቸው።