በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ 1ኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቲፒ ጋር ለሚያደርገው የመልስ ጨዋታ 23 የልኡካን ቡድን በመያዝ ነገ ጠዋት ወደ ዲ.ሪ. ኮንጎ ሉሙምባሺ ያመራል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነገ ጠዋት 1:00 ላይ የኮንጎ ጉዞውን ሲጀምር 18 ተጫዋቾች እና 5 የአሰልጣኝ እና ህክምና ቡድን አባላትን ይዞ ያመራል፡፡ ሉሙምባሺ እንደደረሱም ቀድሞ በተዘጋጀላቸው ሆቴል አርፈው ልምምድ ያደርጋሉ፡፡ ክለቡ ተጨማሪ የክለቡ ሰዎችን ቅዳሜ ጠዋት የሚጓዝ ሲሆን እንደ ሲሸልሱ ጉዞ ደጋፊዎችን ይዞ እንደማይጓዝ ታውቋል፡፡ ፈረሰኞቹ ከባህርዳር መልስ በአዲስ አበባ ልምምዳቸውን የቀጠሉ ሲሆን ከተስፋ ቡድኑ ጋር የልምምድ ጨዋታ ያደረጉ ሲሆን ዛሬም የመጨረሻ ልምምዳቸውን ረፋድ ላይ አድርገዋል፡፡
ወደ ኮንጎ የሚያመሩት 18 ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡-
ግብ ጠባቂዎች
ሮበርት ኦዶንግካራ ፣ ዘሪሁን ታደለ
ተከላካዮች
አሉላ ግርማ ፣ አይዛክ ኢሴንዴ ፣ አስቻለው ታመነ ፣ መሃሪ መና ፣ ደጉ ደበበ ፣ አበባው ቡታቆ ፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ
አማካዮች
ምንያህል ተሾመ ፣ ተስፋዬ አለባቸው ፣ ናትናኤል ዘለቀ ፣ በሃይሉ አሰፋ ፣ ምንተስኖስት አዳነ ፣ አቡበከር ሳኒ
አጥቂዎች
አዳነ ግርማ ፣ ራምኬል ሎክ ፣ ጎድዊን ቺካ