
ቡናማዎቹ በዝውውሩ መሳተፍ ጀምረዋል
[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
በዛሬው ዕለት በተከፈተው የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ ተጫዋች አስፈርሟል።
በአሠልጣኝ ካሣዬ አራጌ የሚመራው ኢትዮጵያ ቡና በዘንድሮ የውድድር ዓመት 20 ነጥቦችን በመያዝ በደረጃ ሰንጠረዡ አካፋይ ቦታ ላይ እንደተቀመጠ ይታወቃል። ዓምና በሊጉ ብዙ ግቦችን ሲያስቆጥር የምናውቀው ቡድኑም ዘንድሮ ፊት መስመር ላይ መሳሳቱን ተከትሎ ዛሬ በተከፈተው የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ላይ በመሳተፍ አጥቂ አስፈርሟል። በዚህም በውድድር ዓመቱ መጀመሪያ ለገላን ከተማ ፈርሞ የነበረው ተመስገን ገብረኪዳን ቡናማዎቹን ተቀላቅሏል።
2010 ከጅማ አባ ጅፋር ጋር የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን እንዲሁም 2011 ላይ ከመከላከያ ጋር የጥሎ ማለፍ እና የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን (መስከረም ላይ የተደረገው የ2010 ውድድር) ያገኘው ተጫዋቹም ለቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት የሚያቆጠውን ውል መፈረሙን ክለቡ በማኅበራዊ ገፁ ይፋ አድርጓል።
ተዛማጅ ፅሁፎች
የሴቶች ፕሪምየር ሊግ | መከላከያ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዋሳ ወሳኝ ድል አሳክተዋል
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በተደረጉ አራት መርሐግብሮች ጅምሩን ሲያደርግ መከላከያ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዋሳ ተጋጣሚዎቻቸውን...
የአሰልጣኞች አስተያየት | አዳማ ከተማ 1-1 ድሬዳዋ ከተማ
በሊጉ ለመቆየት ብርቱ ትግል ተደርጎበት ነጥብ በመጋራት ከተጠናቀቀው ጨዋታ ፍፃሜ በኋላ አሰልጣኞች የድህረ-ጨዋታ አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡ አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ - አዳማ...
ከ17 እና ከ15 ዓመት በታች ውድድሮች የሚደረጉበት ቦታ እና ቀን ይፋ ሆኗል
የ2014 ከ17 ዓመት በታች እና ከ15 ዓመት በታች የፓይለት ፕሮጀክት ውድድሮች የሚደረጉበት ከተማ እና ቀን ታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን...
የአዲስ አበባ ከተማ የቡድን አባላት ዝርፊያ ተፈፀመባቸው
በሲዳማ ቡና ሽንፈት ያስተናገድው የአዲስ አበባ ከተማ የቡድን አባላት ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ዝርፊያ እንደተፈፀመባቸው ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች። ረፋድ ላይ በ29ኛ...
የአሰልጣኞች አስተያየት | ፋሲል ከነማ 3-0 ኢትዮጵያ ቡና
በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ወሳኝ ድል ካስመዘገበ በኋላ አሰልጣኞች ኃሳባቸውን አካፍለዋል። አሰልጣኝ ኃይሉ ነጋሽ - ፋሲል ከነማ ስለጨዋታው "ትንሽ...
ሪፖርት | ሙጂብ እና ሱራፌል ከ20 ሳምንታት በኋላ ዐፄዎቹ የሊጉን መሪነት እንዲረከቡ አድርገዋል
ፋሲል ከነማ በሙጂብ ቃሲም እና ሱራፌል ዳኛቸው ጎሎች ታግዞ ቅዱስ ጊዮርጊስ እስኪጫወት ድረስ የሊጉ መሪ ሆኗል። ባሳለፍነው ሳምንት ሀዋሳ ከተማን...