[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
በቅርቡ ከአሰልጣኝ ዘማርያም ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባው ድሬዳዋ ከተማ አአሰልጣኙን በተመለከተ አዲስ ውሳኔ አሳልፏል።
ካሳለፍነው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ ድሬደዋ ከተማን በማሰልጠን የቆዩት አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ቆይታቸውን በማራዘም ለሁለት ዓመት ለማገልገል በያዝነው ዓመት ውላቸውን ማራዘማቸው ይታወቃል። ቡድኑ ሀዋሳ በነበረው ቆይታ በተመዘገበው ውጤት ደስተኛ ያልሆኑት የክለቡ አመራሮች አሰልጣኝ ዘማርያምን በእግድ አቆይተዋቸው የነበረ ቢሆንም በኃላ ላይ ከ20 ዓመት በታች ቡድኑን ዝቅ ብለው እንዲሰሩ ውሳኔ አሳልፎ ነበር። ይህን ውሳኔ በመቃወም አሰልጣኝ ዘማርያም ለፌዴሬሽኑ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ቅሬታቸውን አቅርበው ነበር።
የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ጉዳያቸውን እየተመለከተ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ድሬዳዋ ከተማ ከሁለት ቀን በፊት ባወጣው ደብዳቤ አሰልጣኝ ዘማርያምን ማሰናበቱን አሳውቋል። በደብዳቤው ላይ ክለቡ አሰልጣኙን ወደተመደቡበት ስራ እንዲመለሱ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም ባለመገኘታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ከቡድኑ ጋር ያላቸውን ውል ያቋረጡ መሆኑ ታውቆ ከስራቸው የተሰናበቱ መሆኑን አስታውቋል።