​ብርቱካናማዎቹ አዲስ አሠልጣኝ ለማግኘት ከጫፍ ደርሰዋል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

የምስራቁ ክለብ ድሬዳዋ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ከጫፍ መድረሱን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።

ያለፉትን ዓመታት በውጤት መንገራገጭ ላለመውረድ ሲታገል የቆየው ድሬዳዋ ከተማ በዘንድሮ የውድድር ዓመትም በተመሳሳይ በውጤት ቀውስ ውስጥ እንደሚገኝ ይታወቃል። ይሄን ተከትሎ ከሳምንታት በፊት ከአሠልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ጋር የተለያየው ክለቡ ከሰዓታት በፊት ጊዜያዊ እና ምክትል አሠልጣኞቹንም ከቦታው ማንሳቱን ከሰዓታት በፊት ይፋ አድርጎ ነበር።

                                               

ከዚህም መነሻነት ክለቡ አዲሲ አሰልጣኝ ለመቅጠር እንቅስቃሴ እያደረገ የነበረ ሲሆን አሰልጣኝ ሳምሶን አየለንም ለመቅጠር ከጫፍ መድረሱን አውቀናል። አሰልጣኝ ሳምሶን ከክለቡ አመራሮች ጋር በቅጥሩ ዙርያ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በቅርቡም አንዳንድ የወረቀት ጉዳዮች ከተጠናቀቁ በኋላ የአሰልጣኙ ቅጥር ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
የቀድሞ ታዋቂ ተጫዋች እንዲሁም አሁን በአሰልጣኝ እያገለገሉ የሚገኙት ሳምሶን አየለ ከዚህ ቀደም ዳሽን ቢራ፣ ሐረር ሲቲ  እና ስሑል ሽረን እንዳሰለጠኑ ይታወቃል።