ድሬዳዋ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ሾሟል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ድሬዳዋ ከተማን በቀጣዩ ዓመት ማን በአሰልጣኝነት ይዞት እንደሚቀጥል ታውቋል።

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ደካማ የአንደኛው ዙር ውድድርን ያሳለፈው ድሬዳዋ ከተማ በረፋዱ ዘገባችን ሙሉ በሙሉ የአሰልጣኝ ቡድን አባላትን ማሰናበቱን ዘግበን ነበር። ከዚህ ባለፈም ክለቡ አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን ለመሾም መቃረቡን ገልፀን የነበረ ሲሆን በዚሁ መሰረት አሰልጣኙን በይፋ በአንድ ዓመት ውል መሾሙ ታውቋል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ሐረር ቢራ ፣ ዳሽን ቢራ እና ስሑል ሽረ አሰልጣኝ የነበሩት ሳምሶን ያለፉትን ሁለት ዓመታት ያለ ስራ ካሳለፉ በኋላ ወደ አሰልጣኝነት ተመልሰው የምስራቁን ክለብ ተረክበዋል፡፡ አሰልጣኙ በነገው ዕለት ረዳቶቻቸውን ይፋ የሚያደርጉም ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ከክለቡ ጋር በተያያዘ ከተሰናበቱት የአሰልጣኝ ቡድን አባላት መካከል የነበሩት የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ አምባዬ በፍቃዱ በድጋሚ መመለሳቸው ተሰምቷል።