​የምንተስኖት አዳነ እና የአዳማ ከተማ ጉዳይ ዕልባት አግኝቷል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ያለፉትን ወራት ከክፍያ ጋር በተገናኘ ውዝግብ ውስጥ ገብተው የሰነበቱት አዳማ ከተማ እና ምንተስኖት አዳነ ጉዳያቸው መቋጫ አግኝቷል።

የአማካይ መስመር ተጫዋቹ ምንተስኖት አዳነ በያዝነው ዓመት መስከረም ወር ላይ አዳማ ከተማን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከተቀላቀለ በኋላ ከቅድመ ክፍያ እና ከደመወዝ ጋር በተገናኘ ውዝግብ ውስጥ በመግባት ሲካሰስ መሰንበቱ ይታወቃል። አሁን ባገኘነው መረጃ ምንተስኖት አዳነ እና ክለቡ በፌዴሬሽኑ አሸማጋይነት በዛሬው ዕለት በስምምነት መለያየታቸውን ይጠቁማል።

ከአዳማ ከተማ ጋር እምብዛም ጨዋታዎች ሳያደርግ ያሳለፈው አማካዩ ከሰሞኑ ወደ አንድ የፕሪምየር ሊጉ ክለቡ ለማምራት በሂደት ላይ መሆኑንም ጭምር ሰምተናል፡፡

                     

ያጋሩ