ወላይታ ድቻ ከግራ መስመር ተከላካዩ ጋር ተለያይቷል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

ወላይታ ድቻ ቀሪ ኮንትራት ካለው የግራ መስመር ተከላካይ ጋር በስምምነት ተለያይቷል፡፡

በአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም የሚመራው እና በዘንድሮው የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያውን ዙር ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው ወላይታ ድቻ በሁለተኛው ዙር የሊጉ ጨዋታዎች ራሱን ለማጠናከር እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ክለቡን በአግባቡ አልጠቀማችሁም ላላቸው ሦስት ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የፃፈ ሲሆን ከግራ መስመር ተከላካዩ ዘካሪያስ ቱጂ ጋር በአንፃሩ የስድስት ወራት ኮንትራት እየቀረው መለያየቱን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች፡፡

የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች የጦና ንቦቹን በክረምቱ የዝውውር መስኮት በአንድ ዓመት ውል መቀላቀል ቢችልም በፕሪምየር ሊጉ ከ2 ጨዋታዎች (ተቀይሮ በመግባት) የዘለለ ግልጋሎት መስጠት አልቻለም። ከስድስት ወራት የክለቡ ቆይታ በኋላም ከወላይታ ድቻ ጋር በስምምነት መለያየቱን ለማወቅ ችለናል፡፡