[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ120 ጨዋታዎች ግምገማ የሚደረግበት እና የሁለተኛው ዙር የሊጉ ሙሉ መርሐ-ግብር የሚከወኑበት ሁለት ከተሞች ተለይተዋል፡፡
የ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የበላይነት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የዘጠኝ ሳምንታት እና በድሬዳዋ ስታዲየም የስድስት ሳምንታት በድሞሩ የአስራ አምስት ሳምንታት 120 ጨዋታዎች ተደርገውበት ከቀናቶች በፊት መጋቢት 23 የዙሩ ውድድር መገባደዱ ይታወሳል፡፡ የሁለተኛው ዙር የሊጉ ቀጣይ ጨዋታዎች ከመደረጋቸው አስቀድሞ ክለቦች ከሊግ ካምፓኒው ጋር በጋራ በመሆን የተደረጉ ጨዋታዎች ላይ ግምገማ እና ውይይትን የሚያከናውን ሲሆን ይህም ስነ ስርአት መቼ እንደሚደረግ ይፋ ሆኗል፡፡ በዚህ መሠረት ከአስራ ሁለት ቀናቶች በኋላ መጋቢት 10 ከቀናት በኋላ በሚገለፅ ሆቴል ይህ መርሐ-ግብር አዲስ አበባ ላይ እንደሚከወን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተያያዘ የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎች የሚደረግበት ቦታ ሙሉ በሙሉ ተለይቶ የታወቀ ሲሆን ቀጣይ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ሳምንታ በባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ደግሞ የዘጠኝ ሳምንታት ጨዋታዎች እንደሚደረጉ ሶከር ኢትዮጵያ ማረጋገጥ ችላለች፡፡